ቻርጅ

የኤሌክትሪክ ቻርጆች በቁስ አተም ውስጥ ከሚገኙ እኑሶች ውስጥ የአንድ አንዶቹ የተፈጥሮ ጠባይ ናቸው። ቻርጆች እራሳቸውን የሚገልጡት በሌሎች ሙሌት እኑሶች ላይ በሚያሳርፉት የስበት ወይም ግፊት ጉልበት ነው።

ቻርጅ
አንድ አይነት ቻርጆች ሲገፋፉ፣ የተለያዩ ቻርጆች ይሳሳባሉ

የኤሌክትሪክ ቻርጆች እራሳቸውን በሁለት ክፍል ይከፍላሉ፣ የአንዱ ክፍል አባላት የራሱን ክፍል አባላት ሲገፋ፣ የሌላውን ክፍል አባል ግን ይስባል። እኒህ ክፍሎች ስም ወጥቶላቸው አንዱ ክፍል ፖዚቲቭ (+) ሲሰኝ፣ ሌላው ወገን ደግሞ ነጌቲቭ (- ) ይሰኛል።

የቻርጆች ቁጠባ መርህ

ለብቻ በሚገኝ ስርዓት ውስጥ ያለ የኤሌክትሪክ ፖዚቲቭና ነጌቲቭ ቻርጅ ድምር ውጤት ምንጊዜም አይለወጥም። ወይንም፣ የተጣራ የኤሌክትሪክ ቻርጅ አይፈጠርምም አይጠፋምም። ለምሳሌ በአንድ የጨው ክሪስታል ውስጥ 5 ነጌቲቭ እና 5 ፖዚትቭ ቻርጆች ቢኖሩ፣ በአጠቃላይ ያ ክሪስታል 0 ቻርጅ አለው ይባላል። ክሪስታሉ ከማናቸውም የውጭ ቁሶች ጋር እስካልተነካካ ድረስ 0 ቻርጅ እንዳለው ይቀጥላል። ይሄ መርህ በብዙ ሳይንስ ተሞክሮወች እንደተጋገጠ፣ ምንጊዜም ፀንቶ ይሰራል።

የቻርጆች ጠጣርነት (ኳንተምነት)

ቻርጆች የተሰሩት ከጠጣር እኑስ ቻርጆች እንጂ እንደተፈለገ ከሚከፋፈሉ ፈሳሽ ነገሮች አይደለም። በተፈጥሮ ተለይተው የሚገኙ ቻርጆች ምንጊዜም የኤለመንታሪ ቻርጅ, e = 1.602×10−19 ኩለምብ ኢንቲጀር ብዜቶች ናቸው። ማለት የዚህ ቻርጅ 2 እጥፍ፣ 3 እጥፍ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ እንጅ ለምሳሌ 2.04 እጥፍ ሊሆኑ አይችሉም። (ለዚህ ህግ አንድ ብቻ ተቃውሞ አለ፣ እርሱም ኳርክ ሲሆን የሙሌቱ ብዛት ⅓e ነው። ሆኖም ኳርኮች ለብቻቸው ተነጥለው አይገኙም፣ ይልቁኑ ምንጊዜ በሃድሮን (ፕሮቶን እና ኒውትሮን) ውስጥ ተጣብቀው ነው ሚገኙት)። ፕሮቶን ሙላቱ e ሲሆን የኤሌክትሮን ቻርጅ −e ነው። አንድ ፕሮቶን 2 ሙላታቸው +2/3e እና አንድ -⅓e ኳርኮች አሉት፣ በተቃራኒ አንድ ኒውትሮን ከ ሁለት -⅓e እና አንድ +2/3e ኳርኮች የተሰራ ነው።

የቻርጅ ልኬት

የቻርጅ መለኪያ ኩሎምብ ሲባል ምልክቱም C ነው። 1C ከ6.242e^18ue}} ጋር እኩል ነው። በሌላ ጎን አንድ ኩሎምብ ማለት በአንድ አምፔር ጅረት ውስጥ በ1ስኮንድ የሚያልፍ ቻርጅ ብዛት ነው። የኤሌክትሪክ ቻርጅ ብዘት በ Q ይወከላል። የኤሌክትርክ ሙሌት መጠንን የሚለካው መሳሪያ ኤሌክትሮሜትር ይባላል።

Tags:

ቁስአተምጉልበት

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ሰይጣንሰዋስውዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ1953የኢትዮጵያ ወረዳዎችውክፔዲያየኮርያ ጦርነትባቲ ቅኝትየፀሐይ ግርዶሽሥነ ጥበብየተባበሩት መንግሥታት ድርጅትቀይአይሁድናመስቃንቆለጥድኩላዝግመተ ለውጥአርሰናል የእግር ኳስ ክለብስዕልመጽሐፈ ጦቢትኦሪት ዘፍጥረትጥር ፲፰ሰው ሠራሽ የማሰብ ችሎታቃል (የቋንቋ አካል)ቱርክዲያቆንሶቅራጠስየደም መፍሰስ አለማቆምቀይ ሽንኩርትየቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎችስምሶዶሰን-ፕዬርና ሚክሎንፍቅር እስከ መቃብርስልጤኛሳላ (እንስሳ)ሊቢያየኢትዮጵያ ሕግልብስዊዘርላንድአቡነ ጴጥሮስየዓለም ዋንጫሥነ ዕውቀትየጋብቻ ሥነ-ስርዓትበእውቀቱ ስዩምየጅብ ፍቅርጥናትሞስኮማህበራዊ ሚዲያገንዘብየዮሐንስ ራዕይፍቅርመጽሐፍ ቅዱስተመስገን ገብሬመቀሌየኢትዮጵያ ነገሥታትምሥራቅ አፍሪካጃቫሚያዝያ ፪ዋሽንትሴማዊ ቋንቋዎችአፋር (ብሔር)ጉግልአናናስየኖህ ልጆችመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስሴቶችድሬዳዋየኢትዮጵያ ሙዚቃአለቃ ገብረ ሐናዋናው ገጽ/ለጀማሪወች/ፊደል አጻጻፍፈሊጣዊ አነጋገር ገታሪክ ዘኦሮሞአንጎል🡆 More