ገመሬ (ጎሪላ) አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ አጥቢ እንስሳ ነው።
?ገመሬ | ||||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ | ||||||||||||||
| ||||||||||||||
ገመሬ በጣም ትልቅ የጦጣ አይነት ነው።
በኢትዮጵያ አነጋገር ደግሞ «ገመሬ» ማለት የዝንጀሮች አለቃ ዝንጀሮ ሊሆን ይችላል።
በ478 ዓክልበ. የቀርታግና ንጉሥና መርከበኛ ተጓዥ 2 ሓኖ እስከ ጋቦን ድረስ እንደ ጎበኘ ይታስባል፤ እሱም እንደ ዘገበው በዚያ በአንድ ደሴት በግሪክ «ጎሪላይ» የተባለ በፍጹም ጠጉራምና አውሬ ጎሣ እንዳገኘ ጻፈ፤ ቆዳዎችንም ይዘው ወደ ቀርታግና ተመለሱ። እነኚህ የሰው ልጆች ሳይሆኑ ጦጣዎች እንደ ነበሩ ስለሚታመን፣ ዘመናዊው የጦጣ ወገን ስም «ጎሪላ» (Gorilla) ከዚህ ታሪክ የተወሰደ ነው።
የገመሬ ወገን ሁለት ዝርዮች አሉት፣ በየዝርያውም ሁለት ሁለት ንዑስ ዝርያዎች አሉ። የገመሬ ወገን አባላት፦
እንደ ሌሎች ጦጣ አይነቶች ሳይሆን፣ ገመሬ በመሬት ይውላል ይተኛልና ከፍራፍሬ ይልቅ በብዛት ቅጠላቅጠልን፣ ግንደ ብሌንም ይበላል። ደግሞ ምስጥና ጉንዳን ይበላል። ገመሬዎች ሁሉ ከሌላ ጦጣ አይነቶች ይልቅ እጅግ ቦርጫም ናቸው። የሚበሉት ሓመልማል ብዛት ስለሚበቃቸው፣ ብዙ ውሃ አይጠጡም። ገመሬን የሚበላው ዋና ነጣቂ ግሥላ ነው።
ያደገው ወንድ ጎሪላ አለቃ የብር ቀለም ጀርባ ስላለው «ብር-ጀርባ» ይባላል። ባብዛኛው ጊዜ ገመሬዎች ሰላማዊ ናቸው፣ አንድ ገመሬ ሲቆጣ አትክልት ይጥላልና ደረቱን ይደብድባል። አልፎ አልፎ ግን ብር-ጀርባዎች ለቡድኑ አለቃነት እርስ በርስ እስከ መግደል ድረስ ይታገላሉ።
በጣም ትንሽ የእጅ ምልክት ቋንቋ ለመማር በቂ ብልሃት እንዳላቸው ተመራማሪዎች አሳውቀዋል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ገመሬ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.