ጦቢያ ወይም ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ በአፈወርቅ ገብረ እየሱስ በ፲፱፻ ዓ.ም.
በሮማ የታተመ ሲሆን 90 ገጾች አሉት። በኢትዮጵያ የሥነ ፅሑፍ ታሪክ የመጀመሪያ ልብወለድ መፅሐፍ ለመሆኑ የሚነገርለት ይህ መጽሐፍ በወቅቱ ተነስቶ የነበረውን የአረማውያንንና የክርስቲያኖችን ጦርነት ይተርካል። ደራሲው በመፅሐፉ ውስጥ ስለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም ስለደግነትና ክፋት፣ ስለሀይማኖትና ፍቅር በሰፊው ያትታሉ። መፅሐፉ በተለይ የፍቅርን ሀያልነት ለማሳየትና የሀይማኖት ልዩነት ስላልበገረው ታላቅ ፍቅር በሰፊው ይተርካል። በተጨማሪም ደራሲው በጽሑፉ ውስጥ ሊያስተላልፉ የሞከሩት መልዕክት የሰው ልጅ በባዕድ አምልኮ ተሸብቦ ከመኖር ይልቅ ፈተናና ችግር ቢገጥሙት እንኳን ለእነዚህ ሳይበገር በአንድ አምላክ አምኖ ከጸና ድል ሊያደርግ እንደሚችል ነው። ጦቢያን ወደ እንግሊዝኛ ለመተርጎም ጥረቱ ተጀምሯል። ከዚህ በፊት የመጀመሪያውን የትግርኛ ልብወለድ መጽሐፍ ወደ እንግሊዝኛ የተረጎመው ግርማይ ነጋሽ በሚቀጥሉት ጊዚያት ጦቢያን ለመተርጎም ወደደቡብ አፍሪካ እንደሚያመራ አሳውቁአል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.