2 ቱትሞስ

፪ ቱትሞስ (ግብጽኛ፦ /ጀሁቲመስ/) ዓኸፐረንሬ በጥንታዊ ግብጽ የግብጽ አዲስ መንግሥትና የ18ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን ሲሆን ምናልባት 1501-1487 ዓክልበ.

የገዛ ነበረ።

ቱትሞስ ዓኸፐረንሬ
የ፪ ቱትሞስ ስዕል በካርናክ ቤተመቅደስ
የ፪ ቱትሞስ ስዕል በካርናክ ቤተመቅደስ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1501-1487 ዓክልበ.
ቀዳሚ 1 ቱትሞስ
ተከታይ ሃትሸፕሱት
ባለቤት ሃትሸፕሱት፣ ኢሰት
ሥርወ-መንግሥት 18ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት 1 ቱትሞስ

2 ቱትሞስ የቀዳሚው የ1 ቱትሞስና የንግሥቱ ሙትኖፍረት ልጅ ነበር። የ2 ቱትሞስ ዋና ንግሥት ደግሞ ያባቱና የሌላይቱ ንግሥት አሕሞስ ልጅ ሃትሸፕሱት ነበረች። የ2 ቱትሞስ ቁባት ንግሥት ኢሰት ተባለች፣ እርሷም የተከታዩ 3 ቱትሞስ እናት ሆነች።

ማኔጦን መሠረት ለ13-14 ዓመት እንደ ገዛ ባብዛኛው ይቀበላል። አንዳንድ መምህሮች ግን ዘመኑ ከ3-4 አመት በላይ አይሆንም ይላሉ።

በ፪ ቱትሞስ ዓኸፐረንሬ ዘመን አባቱ ከኩሽ መንግሥት የያዛቸው የኖቢያ ግዛቶች ያምጹበት ነበር፤ እሱ ግን ሥራዊቱን ልኮ አስመለሠው።

የጦር አለቃው አሕሞስ ፐን-ነኽበት ደግሞ «ሻሱ» በተባለ ወገን ላይ ዘምቶ በርካታ ምርከኞች እንደ ያዘ ይላል። እነኚህ በደቡብ ከነዓን የተገኙት የኤዶምያስ ሰዎች ወይም ሌሎች እንደሚሉ ዕብራውያን ነበሩ። በተጨማሪ ሌላ የተገኘ ጽሑፍ እንዳለን ዓኸፐረንሬ በረጨኑ (ሶርያ) እስከ ኒይ ከተማ ድረስ ዘመተ። ወደ ሶርያ የደረሱ በመርከብ ወይም በመሬት እንደ ሆነ አልተገለጸም።

የ፪ ቱትሞስ ተከታይ በይፋ ልጁ ፫ ቱትሞስ ሲሆን እሱ ግን ገና ሕጻን ልጅ ሆኖ የቱትሞስ ንግሥት ሃትሸፕሱት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴው፣ በቅርብም ጊዜ ውስጥ በራስዋ መብት ፈርዖን ተባለች። በ22ኛ ዓመትዋ (1466 ዓክልበ. ግ.) ዓርፋ ያንጊዜ ፫ ቱትሞስ ለብቻው ፈርዖን ሆነ።

ቀዳሚው
1 ቱትሞስ
ግብፅ ፈርዖን
1501-1487 ዓክልበ.
ተከታይ
ሃትሸፕሱት

Tags:

ግብጽኛጥንታዊ ግብጽ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

አፈወርቅ ተክሌኤርትራሥነ ምግባርሮማንያቅኔቤተ ሚካኤልፋይዳ መታወቂያየኖህ ልጆችሀዲስ ዓለማየሁወላይታወምበር ገፍፋርስውሃየኦሎምፒክ ጨዋታዎችለንደንቀለምግራኝ አህመድሶፍ-ዑመርየአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤትክረምትጉግልየደም መፍሰስ አለማቆምጥምቀትሜክሲኮየዓለም የመሬት ስፋትዱባይሎስ አንጄሌስሕፃን ልጅአድዋቱርክተረትና ምሳሌ፡ ዳንኤል አበራመጽሐፈ፡ትምህርት፡ዘልሳን፡አምኅራ።ባክቴሪያቅዱስ ያሬድየማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፩ትዊተርትግራይ ክልልፋሲለደስየተባበሩት የዓረብ ግዛቶችድመትባሕሬንኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንፀሐይፈንገስሱዳንመጽሐፈ ሲራክባሕልገበጣቡሩንዲአልጀብራየኢትዮጵያ ሙዚቃየአለም ፍፃሜ ጥናትጥር 18ፅጌ ማርያም ገብሩ ደስታየይሖዋ ምስክሮችፈረንሣይወይን ጠጅ (ቀለም)ጳውሎስ ኞኞዓፄ ሱሰኒዮስየአክሱም ሐውልትፕላኔትአስናቀች ወርቁኢንጅነር ቅጣው እጅጉኦማንሣህለ ሥላሴየተባበሩት መንግሥታት ድርጅትባህር28 March🡆 More