ሻውሽታታር

ሻውሽታታር ከፓርሻታታር (ወይም ባራታርና) ቀጥሎ በሑራውያን ላይ የነገሡት የሚታኒ መሣፍንት ንጉሥ ነበር። ዘመኑ ምናልባት 1457-1417 ዓክልበ.

ያሕል ነበር።

ሻውሽታታር
ሻውሽታታር
የሻውሽታታር ማኅተም

በኑዚ በተገኘ ሰነድ፣ የሚታኒ ንጉሥ ፓርሻታታር ወይም ፓርሻታር ባረፈበት ዓመት እንደ ተጻፈ፣ ሻውሽታታርም እንደ ተከተለው ይላል። በብዙዎች አስተሳሰብ ይህ ፓርሻታር እና ባራታርና (ፓራታርና) አንድ ንጉሥ ነበሩ። ሌሎች ግን የተለያዩ ነገሥታት ነበሩና ባራታርና ከፓርሻታታር ቀደመው የሚሉ ናቸው።

በሻውሽታታር መንግሥት ግዛት ውስጥ የሚከተሉት ነገሥታት ለርሱ ተገዥ ነበሩ፦ የአራፕኻ ንጉሥ ኢቅቲ-ተሹቡ፣ የሙኪሽ (አላላኽ) ንጉሥ ንቅመፓ፣ የኪዙዋትና ንጉሥ ሱናሱራ።

ግብጽ ፈርዖን 3 ቱትሞስ ዘመቻዎች በተለይ በ1453 ዓክልበ. ከሐለብ ስሜን የሚታኒን ሥራዊት በአርዓና አሸነፈ። በ1446 ዓክልበ. ቱትሞስ ፫ የሚታኒ አምባዎች በቃዴስ ዙርያ አጠፋ።

ከመቶ አመት በኋላ በሚታኒ የነገሠው ሻቲዋዛ ከኬጥያውያን መንግሥት ንጉሥ ሱፒሉሊዩማ ጋር ባደረገው ውል፣ ሻውሽታታር አሦርን ዘርፎ የአሦር ቤተመንግሥት ወርቃም በሮችን ወደ ሚታኒ ዋና ከተማ ዋሹካኒ ወሰዳቸው ይላል። ይህ ምናልባት 1 አሹር-ናዲን-አሔ የአሦር ንጉሥ ሲሆን (1441 ዓግልበ) ከዚያ እስከ 1366 ዓክልበ. ድረስ የአሦር ነገሥታት ደግሞ ለሚታኒ ግዛት ተገዥ ሆኑ።

የቱትሞስ ተከታይ 2 አመንሆተፕ ደግሞ በሚታኒ ሥራዊት ላይ በሶርያ በ1433 እና በ1429 ዓክልበ. ይዘምት ነበር። በ1428 ዓክልበ. ግ. የኬጥያውያን ንጉሥ 1 ቱድሐሊያ ወርሮ ኪዙዋትናን እንደገና ከሚታኒ ያዘ። በ1427 ዓክልበ. ከግብጽና ከሚታኒ ጋር ስምምነት ተደረገ። በ1421 ዓክልበ. ደግሞ ቱድሐሊያ ሐለብን፣ ሙኪሽንና እስከ ዋሹካኒ ድረስ ወርሮ ለጊዜው ያዛቸው።

የሻውሽታታር ተከታይ 1 አርታታማ እንደ ሆነ ይታስባል።

Tags:

ሑራውያንሚታኒባራታርናፓርሻታታር

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ንዋይ ደበበቤተ አማኑኤልነጭጥግየስልክ መግቢያሰሜን ተራራአርሰናል የእግር ኳስ ክለብብረታኝአውስትራልያሳዑዲ አረቢያዓረፍተ-ነገርኢንዶኔዥያኔልሰን ማንዴላበዓሉ ግርማባሕላዊ መድኃኒትባሕር-ዳርናፖሌዎን ቦናፓርትራስጭፈራአፍሪቃቆጮብራዚልኢሳያስ አፈወርቂአውራሪስዋናው ገጽ/ለጀማሪወች/ፊደል አጻጻፍሞትድንጋይ ዘመንዩ ቱብሥነ ጽሑፍቀጭኔውሻነጋሽየሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትገዳዩ ባልሽ የሞተው ወንድምሽኒው ጄርዚየፈረንሳይ አብዮትየሥነ፡ልቡና ትምህርትአበራ ለማሰአት (መሳሪያ)አልበርት አይንስታይንአስራት ወልደየስዝንብየጣሊያን መንግሥት (1861–1946 እ.ኤ.አ.)አርጎብኛእንጦጦፓሪስሊምፋቲክ ፍላሪያሲስደሴሳዳም ሁሴንሀብቷ ቀናሥላሴየኢንዱስትሪ አብዮትስኳር በሽታየኢትዮጵያ ንግድ ባንክየኮምፒውተር፡ጥናትእስያጉራጌየአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤትደቡብ ቻይና ባሕርሰይጣንበገናቆለጥየእስክንድርያ ማስተማርያ ቤትአንጥረኛኮባልትድሬዳዋከንባታጋምቤላ ሕዝቦች ክልልግራዋየጊዛ ታላቅ ፒራሚድአረቄናምሩድብሔርተኝነትየኢትዮጵያ ብርቤተ አባ ሊባኖስ🡆 More