ፈርዖን ማለት የጥንታዊ ግብጽ ንጉሥ ነው። ይህ ከግብጽኛ «ፐር-ዓ» ከ«ፐር» (ቤት) እና «ዓ» (ታላቅ) ወይም «ታላቁ ቤት» ደረሰ። ፐር-ዓ መጀመርያ ቤተ መንግሥት ለማመልከት ሲሆን፣ ከ1400 ዓክልበ.
በኋላ ንጉሡን ፐር-ዓ ይሉት ጀመር። ስለዚህ ከዚያ በፊትም የነገሡት ግብጻዊ ንገሥታት ለምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረት በአብርሐም፣ በዮሴፍ ወይም በሙሴ ዘመን የነበሩት ነገሥታት ደግሞ «ፈርዖን» ተብለዋል። ነገር ግን በታሪክ ላይ ፈርዖን የሚለው ማዕረግ ጥቅም ላይ የዋለው በጥንቱ የግብጽ መንግሥት ከ 2691-2625 ሳይሆን አሊያም በመካከለኛው የግብጽ መንግሥት ከ 2050-1710 ሳይሆን በአዲሱ የግብጽ መንግሥት በ 1570 ነው። ቁርኣንም ፈርዖን ማለት የጀመረበት በአዲሱ የግብፅ መንግሥት በሙሴ ዘመን ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ፈርዖን, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.