የአስረካቢ ጥግ
| | |
ግቤት x ከ ነጥብ c በ δ ርቅት ላይ ካለ, የf(x) ዋጋ ከጥጉ L በ ε ርቀት ውስጥ ይገኛል። . | | ለማናቸውም x > S, አስረካቢ f(x) ከጥግ L በ ε ርቀት ውስጥ ይገኛል |
አስረካቢ f(x) እና ነጥብ c ቢሰጡ፣ አስረካቢው በተሰጠው ነጥብ ላይ ሊኖረው የሚችለው ጥግ እንዲህ ይጻፋል
-
ትርጉሙም xን ወደ ነጥብ c በማስጠጋት የ አስረካቢ f(x) ዋጋን በተፈለገ መጠን ወደ L ማስጠጋት ይቻላል። እንግዲህ " የx ዋጋው ወደ c ሲጠጋ, የf ጥግ L" ነው ይባላል። በጥንቃቄ መታየተ ያለበት፣ በአንድ ነጥብ ላይ አንድ አስረካቢ ያለው ጥግ እና ውጤት አንድ ላይሆኑ ይችላሉ፣ ማለት f(c) ≠ L። እንዲያውም አስረካቢ f(x) በነጥብ c ላይ ትርጉም ላይኖረውም ይችላል። ጥግ፣ አስረካቢው የሚቀርበውን ዋጋ እንጂ የአስረካቢውን ዋጋ አያሰላም።
ምሳሌ
-
እዚህ ላይ f(1) በዜሮ ማካልፈል ስለሚሆን አስረካቢው 1ን ማስረከብ አይችልም። በሌላ አነጋገር አስረካቢው 1 ላይ ትርጉም የለውም። ሆኖም ግን x ወደ 1 እየተጠጋ ሲሄድ, f(x) ወደ 2 እየተጠጋ ይሄዳል። ከላይ የተሰጠውን በስራ ለማሳየት መጀመሪያ x^2-1 መተንተን ያስፈልጋል. [(x-1)(x+1)]/(x-1). ከዛ መጣፋት የሚችሉትን ካጣፋን በሓላ x+1 ይቀራል. በመጨረሻም 1ን በx ቦታ መተካት. ስለዚህ መልሳችን 2 ነው ማለት ነው. f(x)=(2x-1)/x, x-->∞ ከላዪም ከታችም ∞ን ስለሚተጋ -1 ለውጥ አያመታም. ስለዚህ xን በx አጣፍተን መልሳችን 2 ይሆናል ማለት ነው.
f(0.9) | f(0.99) | f(0.999) | f(1.0) | f(1.001) | f(1.01) | f(1.1) |
1.900 | 1.990 | 1.999 | ⇒ ትርጉም የለሽ ⇐ | 2.001 | 2.010 | 2.100 |
ከሰንጠረዡ መረዳት እንደሚቻለው xን ወደ 1 በማስጠጋት አስረካቢ f(x)ን ወደ 2 በፈለግነው መጠን ማስጠጋት ይቻላል። ስለሆነም አስረካቢው በ1 ላይ ያለው ጥግ 2 ነው ይባላል።
ሂሳባዊ የቀኖና ትርጉም
አስረካቢው f(x) በc ላይ ጥግ አለው ሲባል በሂሳብ ቋንቋ እንዲህ ይጻፋል፡ -
|
| የጥግ ቀኖናዊ ትርጉም |
የጥግ ባህሪዎች
- እኩልዮሽ
-
- መደመር
-
- መቀነስ
-
- ማባዛት
-
- ማካፈል
-
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጥግ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.