ያንጎን (ቡርምኛ፦ ရန္ကုန္မ္ရုိ့) አንድ ታላቅ ከተማ በምየንማር (የቀድሞው 'ቡርማ') ነው። የምየንማ ዋና ከተማ እስከ 1998 ዓ.ም.
ነበረ። በመጋቢት 17 ቀን 1998፣ የምየንማ መንግሥት ኔፕዪዶ አዲሱ ዋና ከተማ መሆኑን አዋጀ።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 4,344,100 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 16°47′ ሰሜን ኬክሮስ እና 96°10′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
'ያንጎን' ማለት ከ'ያን' ('ጠላት' ወይም 'ጥላቻ') እና ከ'ኮውን' ('አልቋል') ተወሰደ። ስለዚህ የከተማው ስም 'ጥላቻ (ወይም ጠላቶች) አልቀዋል' ለማለት ነው። መጀመርያ በ6ኛ ክፍለ ዘመን በሞን ሕዝብ ሲመሠረት ስሙ ዳጎን ነበር። በ1745 ዓ.ም. ንጉሡ አላውንግፓያ አውራጃውን አሸንፎ ስሙን ወደ ያንጎን ቀየረው። እንግሊዞችም በ1844 ከተማውን በጦርነት ሲይዙ ስሙን ራንጉን አሉት። ይህ ስም በይፋ በ1981 ዓ.ም. ወደ ያንጎን ተመለሠ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ያንጎን, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.