የብርሃን ፍጥነት በ c ምልከት ሲወከል፣ ለተፈጥሮ ህግጋት ጥናት ከፍተኛ አስተዋጾ ያለው የተፈጥሮ ቋሚ ቁጥር ነው። ብርሃን በቅጽበት ሳይሆን በተወሰነ ፍጥነት እንደሚጓዝ ቀደምት ሳይንቲስቶች የደረሱበት ጉዳይ ነው። የብርሃን ፍጥነት ለብርሃን ብቻ ሳይሆን ለብርሃን ቤተሰብ ለሆኑት ለኮረንቲና ማግኔት ማዕብሎች ያገለግላል። በአሁኑ ዘመን እንደተለካ፣ የብራሃን ፍጥነት በጥልቁ 299,792,458 ሜትር በሰኮንድ ነው። በሌላ አነጋገር አንድ የብርሃን ጨረር ከፀሐይ ተነስቶ መሬት ለመድረስ 8 ደቂቃ ይፈጅበታል ወይም ደግሞ አንድ የብርሃን ጨረር በየአንድ አንዷ ሰከንድ ወደ ሶስት መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ሜትር (300 ሺህ ኪሎ ሜትር) ይጓዛል።
የፀሐይ ብርሃን መሬት ለመድረስ 8 ደቂቃ ከ19 ሰኮንድ ይወስዳል |
ትክክልኛ ዋጋ = 299,792,458 ሜትር በሰኮንድ |
ተቀራራቢ ዋጋ = 300,000 ኪሎሜትር በሰኮንድ |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article የብርሃን ፍጥነት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.