ክላርኔት ዘመናዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። የዚህ መሣሪያ ስያሜ የመጣው et ከምትለው የመጨረሻ ቅጥያ (ትርጉሟ ትንሽ ማለት ነው።) ጋር clarino የሚለውን የጣልያንኛ ቃል (ትርጉሙ ትራምፔት ማለት ነው።) ጋር በማያያዝ ትንሽ ትራምፔት የሚል ትርጉም በመስጠት ነው። ይህ መሣሪያ እንደ [[ሳክሶፎን ሁሉ ባለነጠላ መንፊያ አለው። መሣሪያውን ለመጫወት በመንፊያው ለተፈለገው የድምፅ መጠን የሚመጥን አየር በማስገባት እና በእጅ ጣቶች መሳሪያው ወገብ ላይ ያሉትን ቁልፎች በመጫን የሚወጣውን ድምፅ ውፍረት እና ቅጥነት መመጠን ይቻላል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ክላርኔት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.