ሳክሶፎን አንዳንድ ጊዜም ሳክስ እየተባለ የሚጠራው ዘመናዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። ይህ መሣሪያ በዋናነት የሚሠራው ከነሐስ እና በውስጡ አየርን የሚያስተጋባ ኃይል ያለው ድምፅ እንዲፈጥር ተደርጎ ነው። ይህ መሣሪያ እንደ ክላርኔት ባለ ነጠላ ምላስ መንፊያ አለው። በመሳሪያው ለመጫወት በመንፊያው በኩል አስፈላጊውን ድምፅ የሚመጥን ኃይል ያለው አየር በማስገባት ነው። በመሣሪያው ወገብ ላይ ያሉትን ቁልፎች በእጅ ጣት በመጫን የድምፁን ቅጥነት እና ውፍረት መቀያየር ይቻላል። መሣሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው በቤልጂየማዊው የሙዚቃ ምሁር አዶልፍ ሳክስ ሲሆን የፈጠራ መብቱን (patent) በሕግ ያስመዘገበው ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፰፻፴፰ ዓ/ም ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ሳክሶፎን, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.