ርግ ቬዳ

ሪግ-ቬዳ (ሳንስክሪት፡= ऋग्वेद /ርግቬዳ/ «የምስጋና ዕውቀት» ) በሂንዱ ሃይማኖት ታሪክ ከሁሉ ጥንታዊ የሆነ እምነት ጽሁፍ ነው። የተቀነባበሩበት ቋንቋ በጣም ጥንታዊ የሳንስክሪት አይነት ሲሆን፣ ይህ ቋንቋ የተነገረው ምናልባት ከ1700-1100 ዓክልበ.

ያህል እንደ ሆነ ይታመናል። የጽሕፈት እውቀት (ዴቫናጋሪ ፊደል) ከዚያ በኋላ ወደ ሕንድ የደረሰው ሲሆን፣ ግጥሞቹ በቃል ድምጽ ብቻ ተወርሰው እንደ ታወሱ ይታመናል። በአሥር መጻሕፍት ወይም «መንደላ» ይከፈላሉ፤ ከነዚህም፣ መንደላዎቹ 2-7 ከሁሉ ጥንታዊ እንደ ሆኑ ይታመናል።

ርግ ቬዳ
Rigveda

ግጥሞቹ ባብዛኛው አርያኖች በዚያን ጊዜ የታመኑባቸው አማልክት ምስጋና መዝሙሮች ናቸው፤ ከነዚህ አማልክት ዋናዎቹ ኢንድራ፣ ሚትራና አግኒ («እሳት») ናቸው። ሌሎች የተፈጥሮ ባሕርዮች እንደ ጣኦታት እራሳቸው ከፍ ከፍ ተደረጉ፦ ቨሩና (ውሃ)፣ ሱርያ (ፀሐይ)፣ ቫዩ (ንፋስ)፣ ድያውስ (ሰማይ)፣ ፕርጢቪ (ምድር) ናቸው። ከነዚህም ጣኦታት፣ የኢንድራ፣ ሚትራ፣ ቨሩና ወዘተ. ስሞች ደግሞ በሚታኒ ጽላቶች (ከ1500-1300 ዓክልበ. ሶርያ አካባቢ) ተገኝተዋል፤ ሚጥራ በተጨማሪ በአቨስታ (የፋርስ ዞራስተር ሃይማኖት መጽሐፍ) ይገኛል። እነዚህ ሁለት ብሔሮች፣ ሚታኒ እና ጥንታዊ ፋርስ፣ በርግ ቬዳ መሠረት ሕንድን ከወረሩት አርያን ወይም ሳንስክሪት ነገዶች ጋራ በቋንቋም ሆነ በእምነት በኩል ቅርብ ዝምድና እንደ ነበራቸው ግልጽ ነው።

:

Tags:

ሂንዱ ሃይማኖትሳንስክሪትእምነት ጽሁፍ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ቅዱስ ሩፋኤልእርሳስሚስቶች በኖህ መርከብ ላይሶሌየራይት ወንድማማችፊሊፒንስራስ መኮንንወልቂጤቦሪስ ጆንሶንአሦርታሪክየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችወንጪንግድአውስትራልያብሉይ ኪዳንፋሲካጤፍየመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊነትየኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርዛጔ ሥርወ-መንግሥትአሸንድየኦገስትጆሮ ጠቢ በሌለበትም ዘንድ ጠብ ጸጥ ይላልኤምኔምጎሽሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥትቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለችታንዛኒያቡዲስምኪርጊዝስታንውቅያኖስጴንጤከባቢ አየርfomgqዒዛናመንግሥተ ኢትዮጵያኤሌክትሪክ ምድጃ ፡ እራስህ ስራጃትሮፋሊቨርፑል የእግር ኳስ ክለብቋንቋአላህአንዶራደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልሳማወላይታመድኃኒትሜታ (ወረዳ)ምግብበርክዋሜ ንክሩማህመጽሐፍ ቅዱስሰለሞንአንድ ፈቃድወሲባዊ ግንኙነትቭላዲሚር ፑቲንአስርቱ ቃላትኢየሱስ ጌታ ነውአዋሳይስማዕከ ወርቁየአፍሪቃ አገሮችቡታጅራተረትና ምሳሌቂጥኝኑግ ምግብቦትስዋናብጉርአባታችን ሆይዶሮ ወጥገብስጁፒተርየአሜሪካ ዶላርሲዳማየምድር መጋጠሚያ ውቅርኢትዮጵያወጋየሁ ደግነቱ🡆 More