መካ የሙስሊሞች ቅድስት ከተማ ስትሆን ካዕባ በመባል የሚታውቅ የአላህ ቤት ያለባትና በእስላም ልማድ «የዱአለም እምብርት» የተባለች ነች። «የአለም እምብርት» በትክክለኛው ይህ ካዕባ የሚባለው መስጅድ አለሃረም ያለበት ቦታ ነው። በዚህ ክልል ማንኛውም አይነት ወንጀል መስራቱ ቅጣቱ ድርብ ነው። አደን ማደን እና ነፍስ መግደል ዛፍ መቁረትም ቢሆን ፈጽሞ የተከለከለ ነው። በመካ በሚገኘው መስጊድ መስገድ ሌሎች መስጊዶች ከሚደረግ ሰላት በአንድ መቶሽ ጊዜ ይበልጣል። የወደቀ ገንዘብ አገኘሁ ተብሎ አይወሰድም ፡ለመስጊዱ አስተዳደር ማስረከብ ይገባል እንጅ! ሰዎች በአለም ዙሪያ ለሃጅ እና ኡምራ ወደዚህ ከተማ ይጎርፋሉ፤ ምክንያቱም ካዕበቱል ሙሸረፋ ወይም ሃረም በመባል የሚታወቅ የአላህ ቤት መሆኑን ያምናሉ። በቁርዓን ዘንድ፣ ይህ የአላህ ቤት በኢብራሂምና በልጃቸው እስማኤል የተገነባ ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article መካ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.