ላፓዝ (La Paz) የቦሊቪያ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1997 ዓ.ም.) 1,250,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 16°30′ ደቡብ ኬክሮስ እና 68°10′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
የጥንቱ ኗሪዎች በሥፍራው ቹቂያፑ (ማለት 'የወርቅ እርሻ' በቀቿ) የተባለ መንደር ነበራቸው። ከተማው ንዌስትራ ሴኞራ ዴ ላ ፓዝ (እስፓንኛ፣ 'የሰላም እመቤታችን') ተብሎ በስፓኒሾች በ1541 ዓ.ም. ተሠራ። በ1817 ዓ.ም. ከአያኩቾ ውግያ በፔሩ ቀጥሎ፣ ስሙ ላፓዝ ዴ አያኩቾ ('የአያኩቾ ሰላም') ተደረገ።
በ1890 ዓ.ም. የመንግሥት መቀመጫ ከሱክሬ ወደ ላፓዝ ተዛወረ። ይሁንና በሕጋዊ ረገድ (በስም ብቻ) ሱክሬ እስከ ዛሬ ድረስ ዋና ከተማነቱን ይዟል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ላፓዝ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.