ፋይኮሎጂ

ፋይኮሎጂ የሚለው ቃል «የባህር አረም» የሚል ትርጓሜ ካለው (φῦκος) /ፉኮስ/ ከተሰኘ የጥንታዊ ግሪክ ቃል እና «ጥናት» የሚል ትርጓሜ ካለው (-λογία) /ሎጊያ/ ከተሰኘ የግሪክ ቃል ጥምረት የመጣ ሲሆን የዋቅላሚዎች ሳይንሳዊ ጥናት ማለት ነው። አልጎሎጂ በመባልም ይታወቅ የነበር ሲሆን ፋይኮሎጂ የሥነ-ሕይወት ዘርፍ ነው።

ከልፕ
በአውስትራሊያ፣ ታዝሜንያ ፍሬሲኔት ብሄራዊ ፓርክ፣ሃዛርድስ ቤይ ውስጥ የሚገኝ ከልፕ

ዋቅላሚዎች በውሃ ስነ ምህዳር ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ምርት በመሆን ያገለግላሉ። አብዛኛዎቹ ዋቅላሚዎች ውን ኑክለሳውያን, የብርሃን አስተጻምሮ የሚያካሂዱ እና እርጥበት ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ፍጥረታት ናቸወ። ከከፍተኛ ተክሎች የሚለዩት በእውነተኛ ሥሮች፣ ግንዶች ወይም ቅጠሎች የሌላቸው በመሆኑ ነው። አበቦችን አያብቡም። ብዙ ዝርያዎች ነጠላ-ሕዋስ እና ጥቃቅን (ፋይቶፕላንክተን እና ሌሎች ደቂቅ ዋቅላሚዎችን ጨምሮ) ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በአንድ ወይም በሌላ ደረጃ ባለብዙ ህዋሳት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹእንደ ከልፕ እና ሳርጋሰም ያሉ የባህር አረሞች ወደ ትልቅ መጠን ያድጋሉ ።

ፋይኮሎጂ ሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች ወይም ሲያኖባክቴርያ በመባል የሚታወቁትን ቅድመ ኑክለሳውያን ጥናትያካትታል።በርከት ያሉ ጥቃቅን ዋቅላሚዎች እንዲሁ በላይከን ውስጥ እንደ ተደጋጋፊ አካላት በመሆን ይገኛሉ።

ፋይኮሎጂስቶች በአብዛኛው የሚያተኩሩት በለጋውሃ ወይም በውቅያኖስ ዋቅላሚዎች ላይ ሲሆን፣ በተጨማሪ ከእነዚህ ዘርፎች ውስጥ ደግሞ በባልጩት ዋቅላሚዎች ወይም ለስላሳ አካል ባላቸው ዋቅላሚዎች ላይ ሊሰሩ ይችላሉ።

የፋይኮሎጂ ታሪክ

የጥንት ግሪኮችም ሆኑ ሮማውያን ስለ ዋቅላሚዎች ያውቁ ነበር፣ እንደውም የጥንት ቻይናውያን አንዳንድ ዝርያዎችን እንደ ምግብ አድርገው ሲያመርቱ የነበር ቢሆንም፣ የዋቅላሚዎች ሳይንሳዊ ጥናት የተጀመረው በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ በ1757 በፔር ኦስቤክ አማካኝነት ፉከስ ማክሲመስ (አሁን ኤክሎኒያ ማክሲማ) ለተባለው ዝርያ ገለጻ እና ስያሜ በመስጠት ነበር።ይህን ተከትሎ እንደ ዳውሰን ተርነር እና ካርል አዶልፍ አጋርድ ባሉ ምሁራን የተሰራ ገላጭ ስራ ነበር፤ነገር ግን በዋቅላሚዎች ውስጥ ጉልህ ቡድኖችን የመፍጠር ሙከራዎች የተደረጉት በ19 ኛው ክፍለ ዘመን ማገባደጃ በጄቪ ላሞሮክስ እና በዊልያመ ሄንሪ ሃርቪ ነበር፡፡ ሃርቪ ዋቅላሚዎችን በቀለማቸው ላይ በመመስረት ወደ አራት ዋና ክፍሎች ስለመደበ በከፊል"የዘመናዊው ፋይኮሎጂ አባት" ተብሎ ተጠርቷል፡፡

በ19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ እና በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ ነበር ፋይኮሎጂ የራሱ ችሎ እውቅና ያለው መስክ የሆነው። እንደ ፍሬድሪክ ትራውጎት ኩትዚንግ ያሉ ሰዎች ገላጭ ስራውን ቀጥለው ነበር። በጃፓን ከ 1889 ጀምሮ ኪንታሮ ኦካሙራ ስለ ጃፓን የባህር ዳርቻ ዋቅላሚዎች ዝርዝር መግለጫዎችን ብቻ ሳይሆን ስለ ስርጭታቸውም አውዳዊ ትንታኔ ሰጥቷል።

ምንም እንኳን አርኬ ግሬቪል አልጌ ብሪታኒኬን በ1830 ያሳተመ ቢሆንም፣ የመለያ ቁልፎች ዝግጅት፣ ሲስተማቲክ ኮሪሌሽን እና ሰፊ የስርጭት ካርታ ስራ የብሪታንያ የባህር ውስጥ ዋቅላሚዎች ካታሎግ በ1902 በአርነስተ ውስጥ በኤድዋርድ አርተር ሊዮኔል ባተርስ እስከታተመበት ጊዜ ድረስ አልነበረም።

ከ1899-1900, አና ዌበር-ቫን ቦሴ የደች ፋይኮሎጂ ባለሙያ የሲቦጋ ጉዞን ከተጉዋዘች በኋላ በ 1904 “ዘ ኮራሊናሲዬ ኦፍ ዘ ሲቦንጋ ኤክስፔዲሽን”  የተሰኘውን ህትመት አሳትማለች።

እ.ኤ.አ. በ 1803 ዣን ፒየር ቫውቸር በዋቅላሚዎች ውስጥ ስላለው አይሶጋሚ(ጾታዊ ግንኙነት) ያሳተመው ህትመት ነበር፤ነገር ግን የዋቅላሚዎች ስርአተ እርባታ እና እድገት በስፋት መጠናት የተጀመረ በ20ኛው ክፍለዘመን መግቢያ ላይ ነበር። ፊሊክስ ዩዢን ፍሪሽ እ.ኤ.አ. በ1935 እና 1945 ያሳተማቸው የተደራጁ እትሞች ስለዋቅላሚዎች ስነቅርጽ እና ስር አተ እርባታ የታወቁ ነገሮች ተጠናቅረውባቸዋል።ይህን ተከትሎ በ1950ዎቹ በሜሪ ፓርኬ የሚመራ የአካባቢ ማረጋገጫ ዝርዝሮች ዝግጅት በ1931ዱ "ከማንክስ አልጌ" እትሟ ላይ፤እሱን ተከትሎ ደግሞ በ1953 "የብሪታንያ የባህር ዋቅላሚዎች የመጀመሪያ ደረጃ ማረጋገጫ ዝርዝር” በተሰኘው እትሟ ተሰርቷል።

ምንም እንኳን የሊሊ ኒውተን የ1931 መመሪያ መጽሃፍ ለብሪታንያ ደሴቶች ዋቅላሚዎች የመጀመሪያውን የመለያ ቁልፍ ያቀረበ ቢሆንም የእንደዚህ ዓይነቶቹ ቁልፎች መደበኛ የሆኑት ገና በ1960 ዎቹ ነበር።በ1980ዎቹ በስነ ምህዳር ላይ በአዲስ መልኩ ትኩረት መደረጉ በዋቅላሚዎች ስብስብ ላይ እና በትላልቅ እጽዋት ስብስብ ውስጥ ዋቅላሚዎች ስላላቸው ስፍራ ተጨማሪ ጥናት ተደርጓል፤ እናም አካባቢአዊ ልዩነቶችን ለማስረዳት ተጨማሪ መሳሪያ አቅርቧል።.

እጅግ የበለጸገ የባህር አረም ያላት አህጉር አውስትራሊያ ስትሆን ወደ 2,000 የሚሆኑ ዝርያዎች ያሏት።

ታዋቂ ፋይሎጂስቶች

  • ኢዛቤላ አቦት(1919–2010)
  • ካርል አዶልፍ አጋርድ(1785-1859)
  • ጃኮብ ጆርጅ አጋርድ(1813-1901)
  • ኤም ኤስ ባላክሪሽናን(1917-1990)
  • ኤልሲ ኤም በሮውስ(1913–1986)
  • ማርጋሬት ኮንስታንስ ሄለን ብላክለር(1902-1981)
  • ኤልሲ ኮንዌይ1902-1992)፣ የብሪቲሽ ፋይኮሎጂካል ሶሳይቲ ፕሬዝዳንት1965-1967።
  • ኢ. ዬል ድውሰን(1918-1966)
  • ጆቫኒ ባቲስታ ዴ ቶኒ(1864-1924)
  • ካትሊን ማርያም ድሩ-ቤከር(1901-1957)
  • ሲልቪያ አሊስ ኤርሌ(1935-)
  • ናትናኤል ሊዮን ጋርድነር(1864-1937)
  • ሮበርት ኬይ ግሬቪል(1794-1866)
  • ሚካኤል ዲ ጊሪ(1949-)
  • ሊና ትሬሲ ሀንክስ(1879–1944)
  • ኤም. ኦ. ፒ ላየንጋር(1886-1986)
  • ኢፊዮን ጆንስ (1925-2004)
  • ቫሱዴቫ ክሪሽናሙርቲ(1921-2014)
  • ፍሬድሪክ ትራውጎት ኩትዚንግ(1807-1893)
  • ማሪ ሊሞይን(1887-1984)
  • ዳያን ኤስ.ሊለር(1945-)
  • ሃንስ ክርስቲያን ሊንግቢ(1782-1837)
  • ካሮላ ኢቬና ሚክል(1900-1970)
  • አይሪን ማንቶን(1904-1988)
  • ቫለሪ ሜይ(1916-2007)
  • ካርል ንጌሊ(1817-1891)
  • ሊሊ ኒውተን(1893-1981)
  • ፍሬድሪክ ኦልትማንስ(1860-1945)
  • ዊሊያም ጄ ኦስዋልድ(1919-2005)
  • ሜሪ ፓርክ(1908-1989)
  • ፍራንዝ ጆሴፍ(1814-1870)
  • ዊልያም አልበርት ሴቼል(1864-1943)
  • ፖል ሲልቫ (1922-2014)
  • ጊልበርት ሞርጋን ስሚዝ(1885-1959)
  • ጆን ስታክሃውስ (የእጽዋት ተመራማሪ) (1742-1819)
  • ዊልያም ራንዶልፍ ቴይለር(1895-1990)
  • ቪቶር ቤኔዴቶ አንቶኒዮ ትሬቪሳን ደ ሴንት-ሊዮን።(1818-1897)
  • ጋቪኖ ትሮኖ ፣ (1931-) ፊሊፒናዊ የባህር ውስጥ ባዮሎጂስት በባህር ውስጥ አረም ላይ ምርምር ለማድረግ ተጠቅሷል።
  • ማሪን ዴ ቫሌራ(1912-1984)
  • አና ዌበር-ቫን ቦሴ(1852-1942)
  • ጆርጅ ስተፈን ዌስት (1876-1919)
  • ዊልያም ዌስት (የእጽዋት ተመራማሪ) (1848-1914)
  • ዊልያም ዌስት ጁኒየር(1875-1901)
  • ካርል ሉድቪግ ዊልደንኖቭ (1765-1812)

ዋቢ ምንጮች

Tags:

ሥነ-ሕይወትዋቅላሚግሪክኛ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

መጽሐፈ ጥበብሸለምጥማጥየኢትዮጵያ ካርታ 1936ቅድስት አርሴማነፍስ1952የአሜሪካ ብሔራዊ ጦርነትመብረቅገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲየአፍሪቃ አንድነት ድርጅትአስቴር አወቀፋርስአክሊሉ ለማ።ዓፄ ቴዎድሮስየርሻ ተግባርሞዚላ ፋየርፎክስአፍሮ እስያዊ ቋንቋዎችገብርኤል (መልዐክ)771 እ.ኤ.አ.የጁ ስርወ መንግስትአቡጊዳፈረንሣይሥርዓተ ነጥቦችፕዌርቶ ሪኮየይሖዋ ምስክሮችወርቃማው ሕግነፃነት መለሰየማርያም ቅዳሴጥላ ብዜትራያሀበሻፈሊጣዊ አነጋገር እመጽሐፈ ጦቢትንግድአረቄኢስታንቡልአዲስ አበባሰባአዊ መብቶችፈንገስየወታደሮች መዝሙርአፄፀጋዬ እሸቱሳህለወርቅ ዘውዴየተፈጥሮ ሀብቶችኒንተንዶJanuaryጉዛራፖሊስሐረግ (ስዋሰው)የአፍሪቃ አገሮችኢትዮጲያየማርቆስ ወንጌልበላይ ዘለቀየዮሐንስ ወንጌልየኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርክዋሻማዲንጎ አፈወርቅ1996ሥነ ሕይወትዘጠኙ ቅዱሳንጊዜመንግሥተ አክሱምጂዎሜትሪመጽሐፈ ሲራክአንበሳ1 ሳባድንችቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያጳውሎስሀይቅሕፃን ልጅነብርየጭቃ እሾህዛምቢያዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ🡆 More