የ2020 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ

ይህ ገጽ የ2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ይዟል።

ጊዜአዊ ሂደት

መጋቢት 2012

በመጋቢት 4 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 13 ቀን 2020) በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ መኖሩ ተረጋገጠ። ግለሰቡ የ48 ዓመት የጃፓን ዜጋ ሲሆን ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች የመለየት እና ክትትል የማድረግ ሥራ እየተካሄደ እንደሆነ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በዕለቱ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ሁኔታዎች በሌሎች አገሮች እየተባባሱ ቢመጡም ኢትዮጵያ የጉዞ እገዳ እንደማታደርግ አስታውቃለች። ቫይረሱ በ134 አገራት ውስጥ ቢኖርም የጉዞ እገዳ ማድረግ ግን እንደማይሰራ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

በመጋቢት 6 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 15 ቀን 2020) ሌሎች ተጨማሪ 3 ዜጎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት አስታውቋል። ሦስቱ ግለሰቦች በመጋቢት 4 ቀን በበሽታው መጠቃቱ ከታወቀው ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን አንዱ የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ የ44 እና የ47 ዓመት የጃፓን ዜጎች ናቸው።

በመጋቢት 7 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 16 ቀን 2020) አንድ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የገባ የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ግለሰብ በቫይረሱ መጠቃቱ ተገልጿል።

በመጋቢት 8 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 17 ቀን 2020) ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የመጣች እንግሊዛዊት ዲፕሎማት በተደረገላት ምርመራ በቫይረሱ መጠቃቷ ተገልጿል።

በመጋቢት 10 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 19 ቀን 2020) ሦስት ተጨማሪ ግለሰቦች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ። አንደኛዋ ግለሰብ የ44 ዓመት ጃፓናዊት ስትሆን መጀመርያ ቫይረሱ እንዳለበት ከተገለጸው ጃፓናዊ ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበራት ነች። ሌላኛው ግለሰብ ደግሞ በመጋቢት 6 ቀን 2012 (እ.ኤ.አ. ማርች 15 ቀን 2020) ወደ ኢትዮጵያ የመጣ የ39 ዓመት ኦስትሪያዊ ነው። ሦስተኛዋ ግለሰብ የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በየካቲት 23 ቀን 2012 (እ.ኤ.አ. ማርች 2 ቀን 2020) ነበር።

በመጋቢት 13 ቀን 2012 (እ.ኤ.አ. ማርች 22 ቀን 2020) ሁለት ተጨማሪ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው ተገለጸ። አንደኛው ከቤልጂየም ወደ ኢትዮጵያ በመጋቢት 5 ቀን 2012 የመጣ የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ በመጋቢት 10 ቀን 2012 የመጣ የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ነው።

በመጋቢት 15 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 24 ቀን 2020) አንድ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ በመጋቢት 10 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 19) የመጣ የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ በቫይረሱ መያዙ ተገለጸ።

በመጋቢት 18 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 27 ቀን 2020) አራት ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል። አንደኛው ኬዝ የ72 ዓመት ሞሪሸስያዊ ግለሰብ ሲሆኑ በመጋቢት 5 (እ.ኤ.አ. ማርች 14) ቀን ከኮንጎ ብራዛቪል የተመለሱ ናቸው። ሁለተኛው ገለሰብ ደግሞ የ61 ዓመት የአዳማ ነዋሪ ሲሆኑ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው። ነገር ግን ከሥራቸው ፀባይ አንጻር ከወጭ ሀገር ዜጋ ጋር ግንኙነት ነበራቸው። ሦስተኛዋ ደግሞ የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን መጋቢት 12 (እ.ኤ.አ. ማርች 21) ቀን ከእስራኤል የተመለሰች ናት። አራተኛዋ ግለሰብ ደግሞ የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ አልነበራትም። ይህንንም ተከትሎ በአገሪቱ በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ግለሰቦችን ቁጥር ወደ 16 ከፍ ብሏል።

በመጋቢት 19 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 28 ቀን 2020) በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል አንዱ ሙሉ በሙሉ ማገገሙ ተገለጸ።

በመጋቢት 20 ቀን (እ.ኤ.አ. ማርች 29 ቀን 2020) አምስት ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል። አንደኛዋ ታማሚ የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን በመጋቢት 8 ከቤልጂየም እና በመጋቢት 10 ደግሞ ወደ ካሜሩን የጉዞ ታሪክ ነበራት። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ታማሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ የ14 ዓመት ወንድ እና የ48 ዓመት ሴት የሆኑ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው። አራተኛው እና አምስተኛው ኬዝ ደግሞ የ38 ዓመት እና የ36 ዓመት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በተለያየ ጊዜ ወደ ዱባይ ተጉዘው እንደነበር ተገልጿል።

በመጋቢት 21 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሠጡት መግለጫ ተጨማሪ 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልጸዋል። አንደኛው ከአሜሪካ የመጣ የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን አንደኛዋ ደግሞ ከዱባይ የመጣች የ37 ዓመት ኢትዮጵያዊት ናት። ሁለቱም የአማራ ክልል ነዋሪዎች ናቸው።

በመጋቢት 22 ቀን አራት ተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል። ሁለቱ ከዱባይ የመጡ የ30 እና የ36 ዓመት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንደኛዋ ደግሞ ከፈረንሳይ የመጡ የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት ናቸው። ይህንንም ተከትሎ ባሁኑ ወቅት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ደርሷል። አራተኛው ታማሚ ደግሞ በመጋቢት 9 ቀን ወደ ኢትዮጵያ የመጣ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ነው።

በመጋቢት 23 ቀን 2012 ሦስት የኮሮናቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል። ሦስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያውያን ናችው። የመጀመሪያዋ ግለሰብ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ጅቡቲ፣ ብራዚል፣ ህንድ እና የመጨረሻ በረራዋ ኮንጎ ብራዛቪል ነው። ሁለተኛው ደግሞየ 26 ዓመት ወንድ ሲሆን ምንም ዓየነት የጉዞ ታሪክ የለውም። ሶስተኛው የ32 ዓመት ወንድ ሲሆን ቀደም ብሎ በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ ክትትል ሲደረግለት የነበረ ነው።

በመጋቢት 24 ቀን አንድ ታማሚ ሙሉ በሙሉ ማገገሙ ተገለጸ። ይህም በአገሪቱ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ የሰዎች ቁጥርን ወደ 3 ከፍ አድርጎታል፡፡

በመጋቢት 25 ቀን ስድስት ተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል፡፡ ስድስቱም የቫይረሱ ተጠቂዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አምስቱ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ አንዷ ደግሞ ከድሬዳዋ ነች፡፡

በመጋቢት 26 ቀን ሦስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ። ሦስቱም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሁለቱ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ በተለያየ ቀን የገቡ ሲሆኑ አንዷ ደግሞ ከስዊድን የገባች መሆኑ ተገልጿል።

በመጋቢት 27 ቀን አምስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ። ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ አንድ ኤርትራዊ እና አንድ ሊብያዊ መሆናቸው ተገልጿል። በዚሁ ዕለትም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ ህልፈቶች ተመዝግበዋል። አንደኛዋ ሟች የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ ከፈረንሣይ በመጋቢት 22 ቀን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ነበሩ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የ56 ዓመት ኢትዮጵያዊ እና ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ ያልነበራቸው ነበሩ።

በመጋቢት 28 ቀን አንድ የ65 ዓመት የዱከም ነዋሪ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተገለጸ።

በመጋቢት 29 ቀን ስምንት ተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ኬዞች ተመዝግበዋል። ሰባቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ኤርትራዊ ነው። ከተያዙት ሰዎች መካከል የ9 ወር ሕጻን ልጅ እንደሚገኝበት ተገልጿል።

በመጋቢት 30 ቀን ሦስት ተጨማሪ ኬዞች ሪፖርት ተደርገዋል። ሁለቱ ወደ ዱባይ የጉዞ ታሪክ ያላቸው የ29ዓመት ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ምንም የጉዞ ታሪክ የሌለው የ36 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያዊ ከአዲስ ቅዳም አማራ ክልል ነው።

ሚያዝያ 2012

በሚያዝያ 1 ቀን አንድ የ43 ዓመት ካናዳዊ በቫይረሱ መያዙ ተገለጼ።

በሚያዝያ 2 ቀን ዘጠኝ ተጨማሪ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል። ሰባቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ የሕንድ እና የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ናቸው። ሁሉም ግለሰቦች የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ አላቸው። በዚህም ቀን ሦስተኛው ሞት ተመዝግቧል። በመጋቢት 28 ቀን በቫይረሱ መጠቃታቸው የተገለጸው የ65 ዓመት የዱከም ነዋሪ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። ይህም በአገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን አጤቃላይ ቁጥር ወደ 3 ከፍ አድርጎታል።

ተጨማሪ መረጃዎች

ዋቢ ምንጮች

Tags:

የ2020 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ጊዜአዊ ሂደትየ2020 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃዎችየ2020 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ዋቢ ምንጮችየ2020 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ2019-20 ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝኢትዮጵያ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

Metshafe henokአብደላ እዝራDሣህለ ሥላሴህሊናመብረቅፓኪስታንየአፍሪካ ቀንድዕውነተኛ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንውክፔዲያኦሪትሰፕቴምበርድንችበዓሉ ግርማአፍሮ እስያዊ ቋንቋዎችቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት1925ጅጅጋኢንዶኔዥያዓለማየሁ ገላጋይአበራ ለማኳታርኦሪት ዘኊልቊየሺጥላ ኮከብዓለም-አቀፍ መደበኛ የመጽሐፍ ቁጥርከፋወርጂእየሱስ ክርስቶስጠጣር ጂዎሜትሪዩክሬንእስስትሥርዓት አልበኝነትደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልስብሐት ገብረ እግዚአብሔርስኳር በሽታየኢትዮጵያ ነገሥታትየወታደሮች መዝሙርኢየሱስሙሉቀን መለሰሕግ ገባግራዋሐረግ (ስዋሰው)ግብረ ስጋ ግንኙነትራያገንዘብደወኒ ግራርመንግሥትየኦሎምፒክ ጨዋታዎችረጅም ልቦለድአማርኛጎጃም ክፍለ ሀገርፌጦሰለሞንቬት ናምደመቀ መኮንንቢልሃርዝያዋናው ገጽ/ለጀማሪወች/ፊደል አጻጻፍየትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴርመሐረቤን ያያችሁኮረሪማፖለቲካሰርቢያአቡጊዳዋሺንግተን ዲሲወልደያታጂኪስታንየኢንዱስትሪ አብዮትሲሳይ ንጉሱአቡነ ተክለ ሃይማኖትአሸንድየእንጎቻጊዜአባይ ወንዝ (ናይል)ወይን ጠጅ (ቀለም)🡆 More