የ2006 እ.ኤ.አ.
ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፰ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፪ እስከ ሐምሌ ፪ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. በጀርመን ተካሄዷል። ከ፮ አህጉሮች ውስጥ ፻፺፰ ሀገሮችን የሚወክሉ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በውድድሩ ተሳትፈዋል። ፴፩ ሀገሮች ማጣሪያውን አልፈው ከጀርመን ቡድን ጋር ለመወዳደር በቅተዋል።
የ2006 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ | |
---|---|
ይፋዊ ምልክት | |
የውድድሩ ዝርዝር | |
አስተናጋጅ | ጀርመን |
ቀናት | ከሰኔ ፪ እስከ ሐምሌ ፪ ቀን |
ቡድኖች | ፴፪ (ከ፮ ኮንፌዴሬሽኖች) |
ቦታ(ዎች) | ፲፪ ስታዲየሞች (በ፲፪ ከተማዎች) |
ውጤት | |
አሸናፊ | ኢጣልያ |
ሁለተኛ | ፈረንሣይ |
ሦስተኛ | ጀርመን |
አራተኛ | ፖርቱጋል |
እስታቲስቲክስ | |
የጨዋታዎች ብዛት | ፷፬ |
የጎሎች ብዛት | ፻፵፯ |
የተመልካች ቁጥር | 3,359,439 |
ኮከብ ግብ አግቢ(ዎች) | ሚሮስላቭ ክሎስ ፭ ጎሎች |
ኮከብ ተጫዋች | ዚነዲን ዚዳን |
← 2002 እ.ኤ.አ. 2010 እ.ኤ.አ. → |
ጣሊያን ለአራተኛ ጊዜ ውድድሩን በማሸኘፍ ድል ተቀናጅቷል። በዋንጫው ጨዋታ ፈረንሳይን ፭ ለ ፫ በቅጣት ምት አሸንፏል። ጀርመን ፖርቱጋልን ፫ ለ ፩ በመርታት ሦስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።
የ2006 እ.ኤ.አ. የዓለም ዋንጫ ብዙ ተመልካቾችን በመሳብ በቴሌቪዥን ታሪክ የሚጠቀስ ነው። ተመልቾች በጠቅላላ 26.29 ቢሊዮን ጊዜ ጨዋታዎቹን እንደተመለከቱ ይገመታል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article የ2006 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.