የአበሻ ስም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚሰጥ ሲሆን አወቃቀሩ ከአረብ እና አይስላንድ አወቃቀር ጋር ተመሳሳይ ነው። አንድ ልጅ ሲወለድ ከሚወጣለት ስም በተጨማሪ በአባቱ እና በአባቱ ወንድ አያት ስም ይጠራል። በተለምዶ አሰያየሙ በአባት በኩል ቢሆንም በኤርትራ ውስጥ በእናት በኩል መሆን እንደሚችል የሚፈቅድ ሕግ ጸድቋል።
የአበሻ ስም እንደ ምዕራባውያን የመጨረሻ ወይም የቤተሰብ ስም (እንግሊዝኛ፦ last name / family name) የለውም። በተጨማሪም ሴቶች ሲያገቡ ስማቸውን አይቀይሩም። በውጭ አገር የሚገኙ ዳያስፖራ አንዳንዴ የአባት ስማቸውን የመሃል ስም (እንግሊዝኛ፦ middle name) እና የአያት ስምን ደግሞ የቤተሰብ ስም አድርገው ይጠቀማሉ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article አበሻ ስም, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.