መንግሥቱ ንዋይ

መንግሥቱ ንዋይ በ፲፱፻፰ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ አራዳ ጊዮርጊስ ገዳም ሠፈር አካባቢ ተወለዱ። አባታቸው ዓለቃ ንዋይ የደብሩ ዓለቃ ነበሩ። ትምሕርታቸውን በተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ተከታትለው አዲሱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ሲመሰረት ወደዚያ ተዛውሩ። የገነት ጦር ትምሕርት ቤት ሲከፈት ደግሞ፣ መንግሥቱ ንዋይ ተመልምለው ከገቡት ዕጩ መኮንኖች አንዱ ነበሩ። ሌሎች (በኋላ ጄነራሎች) እንደነ አቢይ አበበ፣ አሰፋ አያና፣ ኢሳያስ ገብረሥላሴና ከበደ ገብሬ በዚሁ ትምሕርት ቤት ከመንግሥቱ ጋር የነበሩ ዕጩ መኮንኖች ናቸው።

መንግሥቱ ንዋይ

መንግሥቱ ከዚያው የጦር ትምሕርት ቤት በመቶ አለቃ ማዕረግ ተመርቀው ሲወጡ ወዲያው የጠላት ኢጣልያ ጦር አገሪቱን ይወርና እሳቸው ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ወደማይጨው ዘምተው ግዴታቸውን ተውጥተዋል። ጠላትም ድሉን ሲቀዳጅ እና ንጉሠ ነገሥቱ ሲሰደዱ መቶ አለቃ መንግሥቱ በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደሸሸበት ነቀምት ሄደው እዚያ “ጥቁር አንበሳ” የሚባለውን ማኅበር መሥራች አባል ናቸው። ከጥቂት ጊዜም በኋላ ከጓደኞቻቸው ጋር ወደጅቡቲ ተሰደዱ። በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ንጉሠ ነገሥቱ ተመልሰው ካርቱም ሲገቡ እነኚህን ስደተኛ መኮንኖች ከጅቡቲ ወደካርቱም እንዲመጡ ይደረግና መንግሥቱ ንዋይ ከነ ሙሉጌታ ቡሊ፣ ነገሠ ወልደሐና፣ ወልደማርያም ኃይሌ፣ ዘውዴ ገበሳ እና ታምራት ዘገየ ጋር ሆነው ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተቀላቀሉ። ወዲያውም ከእሳቸው ጋር በ፲፱፻፴፫ ዓ/ም አብረው ወደኢትዮጵያ በድል ሲገቡ በክብር ዘበኛ ውስጥ በጄኔራል ሙሉጌታ ሥር ሻምበል ሆነው ቆዩ። በመስከረም ወር ፲፱፻፵፱ ዓ/ም ኮሎኔል መንግሥቱ ብርጋዴር ጄኔራል ተብለው የክብር ዘበኛ ጠቅላይ አዛዥነትን ተሾሙ። ተራማጅ እና የክብር ዘበኛን ሠራዊት በሰገላዊ ውትድርና ንቃተ ሕሊናውን ለማዳበር ብዙ የጣሩ መኮንን እንደነበሩ ተመስክሮላቸዋል።

Tags:

አዲስ አበባገዳም ሠፈር

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ግስጉርጥአፋር (ክልል)የሐበሻ ተረት 1899የተባበሩት የዓረብ ግዛቶችስም (ሰዋስው)ስልጤዳግማዊ ምኒልክየኖህ ልጆችየይሖዋ ምስክሮችገብረ ክርስቶስ ደስታእየሩሳሌምእግር ኳስሀዲስ ዓለማየሁቤተ እስራኤልእስልምናሽፈራውሶቅራጠስወሎአፍሪካሮቦትሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥትየሥነ፡ልቡና ትምህርትበዓሉ ግርማስብሐት ገብረ እግዚአብሔርየሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን2004 እ.ኤ.አ.ዐቢይ አህመድሞሮኮጡት አጥቢየቃል ክፍሎችሊጋባዛጔ ሥርወ-መንግሥትኢንግላንድየዓለም የመሬት ስፋትአቡነ ጴጥሮስተውላጠ ስምመስኮብኛፋይዳ መታወቂያሙላቱ አስታጥቄየማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላትጨዋታዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየፀሐይ ግርዶሽፕዌርቶ ሪኮሃይማኖትሥነ ሕይወትቤተ መርቆሬዎስስነ ምህዳርወንጌልጊዜኃይለማሪያም ደሳለኝየኢትዮጵያ እጽዋትአይሁድናየኣማርኛ ፊደልቁልቋልቤተ ማርያምአማራ (ክልል)ማጅራት ገትርሙሴእንግሊዝኛፈሊጣዊ አነጋገር እሊዮኔል ሜሲሶፍ-ዑመርጊንጥጥቁር ቀዳዳአራት ማዕዘንተረፈ ኤርምያስመጥምቁ ዮሐንስሱዳንማዳጋስካርአምልኮግሥይስማዕከ ወርቁመጽሐፈ፡ትምህርት፡ዘልሳን፡አምኅራ።ኦክታቭ ሚርቦ🡆 More