ግንቦት

ግንቦት የወር ስም ሆኖ በሚያዝያ ወር እና በሰኔ ወር መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ዘጠነኛው የወር ስም ነው።

የግንቦት ቀናት
1 2 3 4 5 6 7
8 9 10 11 12 13 14
15 16 17 18 19 20 21
22 23 24 25 26 27 28
29 30

«ግንቦት» ከግዕዙ «ግንባት» ከሚለው ቃል የተባዛ ነው። የግንቦት ወር የክረምት ጎረቤት ቢሆንም ሙቀታማ፣ ደረቃማ እና ዝንብ የሚበዛበት ወር ነው። በዚህም ጸባዩ ብዙ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን አፍርቷል።

አባቶች "በግንቦት አንድ ዋንጫ ወተት" ይላሉ። ”ኅብረ ብዕር” በተባለው መጽሐፋቸው፣ አቶ ካሕሣይ ገብረ እግዚአብሔር፣ ብሂሉ ሰውነታችን ኃይለኛውን የግንቦት ሙቀት መቋቋም ይችል ዘንድ አንጀት የሚያርስ፣ ቆዳን የሚያለሰልስ፣ የጠፋ አቅምን የሚመልስ ወተት ማግኘት አለበት ለማለት ነው። ይላሉ

ሌላም ብሂል አለ። "በነሐሴ ባቄላ፣ በግንቦት አተላ" የሚለውም ሰው ብቻ ሳይሆን ከብቶችም በደረቃማው ገጽታ ምክንያት በግንቦት ወር ምን ያህል እንደሚጐዱ ያሳያል። በመሆኑም በወሩ አተላ እንደሚወደድ አመልካች ነው።

ግንቦት ጎልታ የምትታወቀው በተለይ ዓመት ካመት ከልደታ ጋር ነው። ልዩ ክብር አላት፤ ድግስም አላት። ከንፍሮ እስከ ቂጣ ብሎም እስከ እርድ ድረስ ይፈጸምባታል።

ኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ ሥርዐት ደግሞ "ቦረንተቻ" የሚከበርበት ወር ነው። ጐጆ የወጣ ሁሉ ከሠላሳ ቀናት በአንዱ (ራሱ በመረጠው) ድግስ መደገስ አለበት፤ በድግሱ መቅረብ ያለባቸው የድግስ ዓይነቶችም ቂጣ፣ ቆሎ፣ ጉሽ ጠላና በግ ናቸው፤ ለድግሱ የሚታረደው በግ፣ ሙሉ ጥቁር ሆኖ ግንባሩ ላይ ነጭ ምልክት ያለበት መሆንም ይኖርበታል። የድግሱ ሥነ ሥርዓት የሚከናወነው ከመሸ በኋላ ማለትም ከብት በረት ከገባ በኋላ ሲሆን፣ ለዝግጅቱ ተብሎ የሚታረደው የበግ ሥጋ መበላት ያለበት ተጠብሶ ነው። ከዚህ ውጭ ሥጋው በወጥ መልክ ተሠርቶ ወይም በጥሬው መብላት አይፈቀድም።


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ

ግንቦት

ግንቦት የወር ስም ሆኖ በሚያዝያ ወር እና በሰኔ ወር መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ዘጠነኛው የወር ስም ነው።

  • "ግንቦት - የኢትዮጵያ መንግሥት መባቻ"፣ በሔኖክ ያሬድ፦ ሪፖርተር (26 May 2010)

Tags:

ሚያዝያሰኔኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ስምሌባየሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል (ኢትዮጵያ)ክዋሜ ንክሩማህኦሞ ወንዝሴቶችቦሌ ዓለም አቀፍ ጥያራ ጣቢያየአክሱም ሐውልትመኪናአሜሪካህሊናአልበርት አይንስታይንየአድዋ ጦርነትደብረ አቡነ ሙሴበርሊንሸዋቀለምኤርትራከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርይስሐቅአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስቅዱስ ያሬድየዓለም የህዝብ ብዛትረጅም ልቦለድአሦርሥርዓተ ነጥቦችኔልሰን ማንዴላኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክየሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀልየቅድስት ድንግል ማርያም ስሞችደወኒ ግራርሀይቅይርዳው ጤናውጥላሁን ገሠሠዓፄ ቴዎድሮስጉራጌቪክቶሪያ ሀይቅደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህየወልወል ጦርነትኮምፒዩተርከነዓን (የካም ልጅ)ጋብቻግብረ ስጋ ግንኙነትጸጋዬ ገብረ መድህንቱርክገዳም ሰፈርርዕዮተ ዓለምፈረንሣይዓርብየአፍሪቃ አገሮችደብረ ሊባኖስአዲስ አበባባክቴሪያሊቨርፑል የእግር ኳስ ክለብኦሪት ዘፍጥረትገብረ መስቀል ላሊበላየደም መፍሰስ አለማቆምየኢትዮጵያ አየር መንገድጥርኝባሕልመጽሐፈ መቃብያን ሣልስገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች ሀአበባ ደሳለኝአቡነ ቴዎፍሎስአክሱም ጽዮንዋሽንትበጌምድርአቡጊዳየምድር እምቧይየኢትዮጵያ ታሪክ፡ ኑብያ አክሱም ዛጉዬ ክፍል ፱/፲፬ንፍሮየእብድ ውሻ በሽታየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትፊሊፒንስ🡆 More