ጄራልድ ሩዶልፍ ፎርድ፣ ጁንየር (እንግሊዝኛ፦ Gerald Rudolph Ford, Jr.፤ ሐምሌ 7 ቀን 1905 ዓ.ም.
- ታኅሣሥ 17 ቀን 1999 ዓ.ም.) ከ1966 ዓ.ም. እስከ 1969 ዓ.ም. ድረስ የአሜሪካ አገር 38ኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። ከዚያ በፊት ከ1965 ዓ.ም. እስከ 1966 ዓ.ም. ድረስ የአገሩ ምትክል-ፕሬዚዳንት ነበሩ። በአሜሪካ ሕገ መንግሥት 25ኛ ማሻሻያ መሠረት ምትክል-ፕሬዚዳንት መጀመርያው የሆነው እሳቸው ነበሩ። ከዚያ በኋላ በነሐሴ 3 ቀን 1966 ዓ.ም. ፕሬዚዳንቱ ሪቻርድ ኒክሰን ማዕረጋቸውን በተዉ ጊዜ በሳቸው ፈንታ አዲስ ፕሬዚዳንት ሆኑ። ከአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች መካከል 5ኛው ያለ ሕዝብ ምርጫ የተመረጡ ሲሆኑ፣ እንደ ፕሬዚዳንት ወይም እንደ ምትክል-ፕሬዚዳንት መቸም ያልተመረጡት ፕሬዚዳንት እሳቸው ብቻ ሆነዋል። በዋተርጌት ቀውስ ጊዜ በመካከሉ የኒክሶንን ፪ኛ ዘመን ፈጸሙ ብቻ እንጂ ሙሉ ዘመን ከገዙት ፕሬዚዳንቶች መካከል አይቆጠሩም።
በ93 ዓመታቸው በሞት ተለዩ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጄራልድ ፎርድ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.