ኪጋሊ የሩዋንዳ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 851,024 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 01°56′ ደቡብ ኬክሮስ እና 30°04′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
ኪጋሊ በ1899 ዓ.ም. በጀርመን ግዛት ተመሠረተ። ሆኖም ሯንዳ ነጻነት በ1953 ዓ.ም. እስከሚያገኝ ድረስ ዋና ከተማ አልነበረም። ከነጻነት በፊት የሟሚ (ንጉሥ) መቀመጫ በንያንዛ ሲሆን የጀርመኖች መቀመጫ በአስትሪዳ (የዛሬ ቡታሬ) ተገኘ።
ከመጋቢት 28 ቀን 1986 ዓ.ም. ጀምሮ በሁቱ እና በቱጺ ነገዶች ላይ በደረሰው ፍጅት አንድ ሚሊዮን ያሕል ሰዎች በኪጋሊ ተገደሉ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ኪጋሊ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.