የካም ልጅ ከነዓን

ከነዓን በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የካም ልጅና የኖህ ልጅ-ልጅ ነበረ። በዛሬው እስራኤልና ሊባኖስ ያለው አገር በጥንት ስለ ስሙ ከነዓን ይባል ነበር።

የከነዓን በኩር ልጅ ሲዶን ሲሆን ሲዶና ከተማ እንደ ተመሠረተና የፊንቄ አባት እንደ ሆነ ተብሏል። እንዲሁም ኬጢ ወይም ኬጢያውያን፣ አሞራዊው ወይም አሞራውያን የተባሉት ሕዝቦች ከከነዓን ተወለዱ። ከዚህ በላይ ኢያቡሳውያን፣ ጌርጌሳውያን፣ ኤዊያውያን፣ ዐሩኬዎን (ዐርካዊው)፣ ሲኒአራዴዎንሰማሪዎን፣ እና አማቲ የተባሉት ዘሮች ከከነዓን ወጡ።

ኦሪት ዘፍጥረት ኖህ በአራራት ተራራ ሰክሮ ስለ ካም ጥፋት ከነዓንን ረገመው። በመጽሐፈ ኩፋሌ ደግሞ ከነዓን ከወንድሞቹ ጋር በግዮን ማዶ ለመስፈር እምቢ ብሎ በአርፋክስድ ሴም ርስት ውስጥ በመቀመጡ ይረገማል።

ኢትዮጵያ ልማዳዊ ታሪክ፣ የከነዓን ልጅ አርዋዲ (አራዴዎን) እና ሚስቱ ኤንቴላ ከእስያ ወደ ኢትዮጵያ በ2108 ዓክልበ. ተሻገሩ። የቅማንት ብሔር ከልጃቸው አናየር እንደ ተወለዱ ይተረካል። ኢትዮጵያ በኩሽ ልጆች በተገዛችበት ዘመን 2 ሌሎች ከነዓናዊ ነገዶች የገቡ ከሲኒ ሻንጉል፣ ከሳምሪ (ሰማሪዎን) ወይጦ መሆናቸው የሚመስክር ልማድ አለ።

አውሮፓ ልማዳዊ ታሪክ ደግሞ፣ የከነዓን ልጅ ዐርካዊው (አርካድ) መጀመርያ በአርካድያ (ግሪክ) ሠፈረ፣ ወንድሙም አማቲ በኤማጥያ (መቄዶን) ሠፈረ። ይህ ከተሞች በሊባኖስ (አርቃሐማት) ከሠሩ በኋላ ነበር ይባላል።

ፋርስ ሊቅ አል-ታባሪ (907 ዓ.ም. ግድም) የተረከው፣ የከነዓን ሚስት አርሳል ስትባል ይቺ የቲራስ ልጅ ባታዊል ሴት ልጅ እንደ ነበረች እርስዋም «ጥቁሮች፣ ኖባውያን፣ ፌዛን፣ ዘንጅ፣ ዛግሃዋህና የሱዳኑ ሕዝቦች ሁሉ» እንደ ወለደችለት ነበር።

Tags:

ሊባኖስመጽሐፍ ቅዱስኖህእስራኤልከነዓን (ጥንታዊ አገር)ካም

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ሀመርቤተ እስራኤልበርበሬጋሞጐፋ ዞንስፖርትእምስአበበ ቢቂላአምሣለ ጎአሉአባይሙቀትጌዴኦጋሊልዮየምድር ጉድኒንተንዶሥርዓት አልበኝነትሰዓት ክልልየኮርያ ጦርነትጥሩነሽ ዲባባቢዮንሴሥነ አካልሮማይስጥዘመነ መሳፍንትሰዋስውደብረ ታቦር (ከተማ)ቁጥርሀዲስ ዓለማየሁማንችስተር ዩናይትድሰምና ፈትልዓሣአዲስ ዘመን (ጋዜጣ)ግብርምሳሌሳህለወርቅ ዘውዴአፋር (ክልል)ማሞ ውድነህጸጋዬ ገብረ መድህንሆሣዕና (ከተማ)ሊኑክስቅኔማሲንቆእንጀራቅዱስ ገብረክርስቶስt8cq6ዝሆንየሮማ ግዛትማሌዢያስብሐት ገብረ እግዚአብሔርስብሃት ገብረእግዚአብሔርሐረርመለስ ዜናዊቴሌብርፈላስፋኦሞ ወንዝግራኝ አህመድዓለማየሁ ገላጋይነጭ ሽንኩርትየምኒልክ ድኩላአበበ በሶ በላ።የእግር ኳስ ማህበርሸዋቀጤ ነክትምህርትሴምአል-ጋዛሊድመትፕሩሲያስሜን አሜሪካስታምፎርድ ብሪጅ (የእግር ኳስ ሜዳ)ባሕልራያመዝገበ ቃላትንዋይ ደበበዕብራይስጥፍቅርአዲስ ነቃጥበብኤችአይቪ🡆 More