ሴም

ሴም (ዕብራይስጥ፦ שֵׁם /ሸም/) በብሉይ ኪዳንና በአይሁድ፣ ክርስቲያንና እስላም ሥነ ጽሑፍ ዘንድ በኖኅ መርከብ ላይ ከማየ አይኅ ካመለጡት ከኖኅ ሦስት ወንድ ልጆች መሃል አንዱ ነው። ወንድሞቹ ካምና ያፌት ነበሩ፤ ልጆቹም ኤላም፣ አሦር፣ አራም፣ አርፋክስድና ሉድ ናቸው።

ሴም
ሴም በ1546 ዓም እንደ ተሳለ

መጽሐፈ ኩፋሌ ዘንድ ሴም በ1207 ዓ.ዓ. ተወለደ፤ በዚህ አቆጣጠር በ1308 ዓ.ዓ. ማየ አይኅ ወይም የጥፋት ውኃ በደረሰበት ዓመት የሴም ዕድሜ 101 ዓመት ያህል ነበር። ሚስቱም ሰደቀተልባብ ተብላ በመርከቡ ላይ ደግሞ አመለጠች። በስምምነት ሴም የተቀበለው የምድር ርስት ዕጣ በእስያ ከጢና ወንዝ (ዶን ወንዝ)ና ከግዮን ወንዝ (አባይ ወንዝ) መካከል ተገኘ። (ስለ ሴም ሚስት ስም በሌሎች ልማዶች ውስጥ፣ ሚስቶች በኖህ መርከብ ላይ ይዩ።)

ሴም
ሴም፣ ካምና ያፌት በ1896 ዓም ስዕል

ኦሪት ዘፍጥረት 11:10 ዘንድ፣ ሴም 100 ዓመት ሲሆን ከጥፋት ውሃ 2 ዓመት በኋላ አርፋክስድን ወለደ፤ ከዚያ ሌላ 500 ዓመት ቆይቶ ባጠቃላይ 600 ዓመታት ኖረ። ይህ ከ2864 እስከ 2264 ዓመት ያህል ድረስ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሊሆን ይችላል።

በልማድ ዘንድ ልጆቹ ኤላምአሦርአራም፣ ከለዳውያንና ልድያ የተባሉትን ጥንታዊ ብሔሮች ወለዱ። እስራኤል፣ አረቦችና አግዓዝያን ከከለዳውያን (አርፋክስድ) ዘር ወጡ። በቋንቋ ጥናት ኤላማውያን ወይም ልድያውያን የሴማዊ ቋንቋ ተናጋሪዎች አልነበሩም፤ የሴም ዘር ያልሆነው የከነዓን ሕዝብ ግን ሴማዊ ቋንቋ ተናገሩ፤ ዘመናዊ ዕብራይስጥም የከነዓንኛ አይነት ይመስላል።

በአንዳንድ የአይሁድ ምንጭ የመልከ ጼዴቅ መታወቂያ በውነት ሴም የኖህ ልጅ ነበረ። በሌሎች ጽሑፎች ውስጥ ግን መልከ ጼዴቅ የሴም ልጅ ልጅ ይባላል።

በእስልምና ሥነ ጽሑፍ ብዙ ጊዜ ሴም (አረብኛ፦ /ሳም/) እንደ ነቢይ ይቆጠራል።

Tags:

ሉድማየ አይኅብሉይ ኪዳንኖኅአሦር (የሴም ልጅ)አራም (የሴም ልጅ)አርፋክስድአይሁድኤላም (የሴም ልጅ)እስላምካምክርስቲያንዕብራይስጥያፌት

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ማርውቅያኖስገብስገጠርየማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላትፕላኔትማሪቱ ለገሰፀሐይ ዮሐንስንብቀጤ ነክኮንሶመጽሐፈ ዕዝራ ካልዕሥነ ጥበብየተፈጥሮ ሕግጋት ጥናትጉሬዛልብነ ድንግልኦሮምኛያህል ነው እንጂመጋቢትአፈርእንደወጣች ቀረችአለማየሁስዕልኦሪትቅዱስ ላሊበላዕብራይስጥጓጉንቸርዓረብኛየጊዛ ታላቅ ፒራሚድየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግሰለሞንሀመርቦብ ማርሊየአድዋ ጦርነትተመስገን ተካጊንጥየሂንዱ ሃይማኖትመሐመድወይን ጠጅ (ቀለም)አብርሀም ሊንከንዋናው ገጽክራርሊዮኔል ሜሲ800 እ.ኤ.አ.አረንጓዴሀዲያጎንደር ዩኒቨርስቲሜሪ አርምዴአባ ጉባ1200 እ.ኤ.አ.ዩ ቱብየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግኢንዶኔዥያጫማ (የርዝመት አሀድ)ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃሱፍየሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል (ኢትዮጵያ)አበራ ለማጥላሁን ገሠሠአምባሰልፍርድ ቤትአቡነ ቴዎፍሎስኖኅድግጣደቡብ ቻይና ባሕርዓሣመርካቶኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያንእንስሳ🡆 More