ከበሮ (ድረም) በእንግሊዝኛው Drum Kit ወይም Drum Set አንዳንዴም trap set እየተባለ የሚጠራው የተለያዩ አይነት የድረም እና የጠፍጣፋ ሠሀን መሣይ የመሣሪያ ዓይነቶችን እንዲሁም በአብዛሀኛው ተያያዥነት ያላቸውን ድምፆች ማፍለቅ የሚችሉ መሣሪያዎችን አጣምሮ የያዘ ዘመናዊ የምት የሙዚቃ መሣሪያ ነው። እነዚህን ስብስቦች እንደ ቀጭን እንጨት ወይም የሙዚቃ መዶሻ አልያም ተመሣሣይ መሣሪያ በመጠቀም መምታት ይቻላል። ይህን መሳሪያ ከበሮ መች (እንግሊዝኛ Drummer) በተገቢው መንገድ መጫወት ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ ባስ ድረም የሚባለው በእግር የሚመታ ፔዳል መዋቅር ያለው ሲሆን ሌላው ደግሞ እርስ በርስ የሚገጣጠሙ ሁለት ስሀኖች በእግር ለመምታት የሚረዳ ፔዳል ያለው ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ከበሮ (ድረም), which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.