ደብረ ብርሃን

ደብረ ብርሃን በሸዋ ክፍለ ሀገር የጅሩ ሸዋ ሜዳ ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ የሰሜን ሸዋ ዞን (አውራጃ) አስተዳደር ርዕሰ ከተማ ከመሆኗ ባሻገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ዋና ጽሕፈት ቤት እዚሁ ይገኛል።

ደብረ ብርሃን
አገር ደብረ ብርሃን ኢትዮጵያ
ክልል አማራ ክልል
ዞን ሰሜን ሸዋ
ከፍታ 2,840 ሜትር
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 50,780
ደብረ ብርሃን is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ደብረ ብርሃን

9°41′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°32′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

፲፱፻፺፰ ዓ/ም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው ደብረ ብርሃን ከተማ የ፷፯ ሺህ ፪፻፵፫ ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም ፴፬ ሺህ ፶፭ ወንዶችና ፴፫ ሺህ ፻፹፰ ሴቶች ይገኙባታል ይላል።

በሌላ ገለልተኛ የግምት ትመና ደግሞ ከተማዋ የ፶፯ ሺህ ፯፻፹ ሕዝብ መኖሪያ እንደሆነች ተገምቷል። የከተማዋ አቀማመጥ በ9°41′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°32′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።

ደብረ ብርሃን ከአዲስ አበባ ፻፴ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደሴ መስመር ላይ የምትገኝ ስሆን ፱ የአስተዳደር ቀበሌዎችም አሏት። የአየር ንብረቷ ደጋማ ነው። የተቆረቆረችውና ስያሜዋን ያገኘችው ደግሞ በ፲፬፻፵፮ ዓ/ም አካባቢ በዓፄ ዘርአ ያዕቆብ (፲፬፻፴፬-፲፬፻፷፰) ነበር። ከተማዋ ድሮ የንጉሡ የግራ በአልቴሃት (ግራ በአልቴሃት ከንጉሡ ሦሥት ሚስቶች የአንደኛዋ የክብር ስም ነው) ርስት ነበረች። በ፲፬፻፵ዎቹ መጀመሪያ አጤው ከእንደግብጣን ወጨጫ ተራራ ማለትም ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ ከነበረው ያባታቸው አጤ ዳዊት መናገሻ ሥፍራ ተነስተው ሲጓዙ በአካባቢው ውበት ስለተደሰቱ የድንኳን ከተማቸውን ከተሙባት። በኋላም ቤተ መንግሥት አሳንፀውና ባለወርቅ ጉልላት የነበረውን የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አሰርተው ቆረቆሯት። "ተአምረ ማርያም" የተሰኘ የጥንት ድርሳን የከተማዋን ስያሜ ከአንድ ተአምራዊ ሁነት ጋር አያይዞ ይገልፀዋል። በ፲፬፻፵፮ ዓ/ም በክርስትና ሃይማኖት ካህናትና በጥቂት የሃይማኖቱ ተከራካሪዎች መካከል ክርክር ይነሳል። ንጉሡና የካህናቱ አለቆች በተገኙበት አንድ ዕለት በጉባዔ ክርክሩ ተካሄደ። በመጨረሻም «እስጢፋኖሳውያን» በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ተከራካሪዎች አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ተጠይቀው አሻፈረን በማለታቸው ከፍተኛ ቅጣት ይደርስባቸዋል።

ይህ በሆነ በ፴፰ኛው ቀን በመጋቢት ፲ ቀን 1446|፲፬፻፵፮ ዓ/ም ረዘም ላለ ጊዜ / ምናልባትም ለቀናት/ የቆየ ቦግ ያለ ብርሃን ከሰማይ ይወርዳል። የብርሃኑ መውረድ ለእስጢፋኖሳውያን ስህተተኛነት ለካህናቱ ደግሞ ትክክለኛነት ምስክር ነው በሚል ተተርጉሟል። ስለዚህ ብርሃን መውረድ የንጉሡ ዜና መዋዕልም ያትታል። በዚህ ሳቢያ ንጉሡ የሥፍራውን ስም ደብረ ብርሃን /የብርሃን አምባ/ በማለት ሰይመውታል።

ይህ መንግስቱ ያመነበት ነግር ነው በብዙዎች ዘንድ የሚታመነው እውነታ ግን በዚያ ግዜ የነበሩ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን እውነተኛውን ኃይማኖት አንክድም ለስዕል አንሰግድን ማለታቸው ነበር ንጉሱን ያስቆጣው

በዚህም ምክንያት ነበር ንጉሱ እስጢፋኖሳውያን እስከ እንገታቸው እንዲቀበሩና በላያቸው የፈረስ ሰራዊት ሄዶባቸው በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ያዘዘው.

ከዚህም የተነሳ የመጣው መብረቅ የመሰለ አስፈሪ ብርሀን

የመጣው የእግዚእብሔር ቁጣ ነበር እንጂ ደስታው አልነበም።

ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ከንግሥና ዘመናቸው ፲፬ ዓመታት የሚሆነውን በደብረ ብርሃን ከተማ እንዳሳለፉና አብዛኛዎቹን የሃይማኖትና የፍልስፍና ድርሰቶቻቸውን የፃፉት በዚሁ ከተማ መሆኑ ይነገራል። በዘመኑም ደብረ ብርሃን ከፍተኛ የትምህርት ማዕከል የነበረች ሲሆን በንጉሡ ትእዛዝ በርካታ የሃይማኖት መፃሕፍት የትርጉም ሥራ ተከናውኖባታል።

በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኣዲስ ኣበባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲጣበቡ ለሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተማሪዎች እንዲያገልግል ኃይለ ማርያም ማሞ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደብረ ብርሃን ተሠራ። ለመጀሪያዎቹ ስድስት ዓመታት ለተማሪዎቹም መጀመሪያ በየወሩ ፳ ብር በኋላም ፲፭ ብር እየተፈልላቸው ነበር የተማሩት። ከምሩቃኖቹም መካከል ዶ/ር ኣበራ ሞላ ታላቅ ወንድማቸው ዶክተር በቀለ ሞላና ታናሽ ወንድማቸው ጌታቸው ሞላ ይገኙበታል።

ማጣቀሻዎች

ምንጭ

  • የአማራ ብሔራዊ ክልል፤ ባህል፣ ቱሪዝምና ማስታወቂያ ቢሮ፤ “የአማራ ክልል የቱሪስት መስህብ ሃብቶች (አጭር ቅኝት)”፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት (፲፱፻፺፩ ዓ/ም)


Tags:

ሸዋየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ኒሺታምራት ደስታጥምቀትጋምቤላ (ከተማ)የተባበሩት ግዛቶችአበራ ለማራስ መኮንንገብስየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንእንጀራእንቆቅልሽየማርያም ቅዳሴ ገፅ ፱ጥናትLዋቅላሚብሳናበ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትዳግማዊ አባ ጅፋርገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች ሀየሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንመጽሐፈ ዕዝራ ካልዕሄፐታይቲስ ኤሂሩት በቀለፍልስፍናፈሊጣዊ አነጋገርጴንጤአቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞጨዋታዎችአቡነ የማታ ጎህደቡብ አሜሪካየታቦር ተራራቦብ ዲለንሴኔጋልባለ አከርካሪኦሮማይአንዶራደማስቆቅድስት አርሴማቅኔአሸናፊ ከበደአምልኮየኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርግድግዳቋሪት«የሰብዓዊ መብት አቀፋዊ መግለጽ»አቡነ አረጋዊአደሬሴባስቶፖል መድፍአብዮትአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭጌታቸው ካሳስብሐት ገብረ እግዚአብሔርቤተ ሚካኤልየኢትዮጵያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎችሰመራፀጋዬ እሸቱመላኩ አሻግሬየቅርጫት ኳስመስተዋድድሾላ በድፍንርዕዮተ ዓለምዋሊያአክሊሉ ለማ።ደርግፀደይብሔርተኝነትቤተ ማርያምቅዱስ መርቆሬዎስሥነ ምግባርቋንቋ አይነትሥልጣኔማሪቱ ለገሰየፀሐይ ግርዶሽ🡆 More