ኦስሮኤኔ

ኦስሮኤኔ (ግሪክኛ፦ Ὀσροηνή ፣ አረማይክ «የኡርኻይ መንግሥት») ከ140 ዓክልበ.

ጀምሮ እስከ 234 ዓም በስሜን መስጴጦምያ የተገኘ ነፃ አገር ግዛት ነበር። ከዚያ በኋላ እስከ 600 ዓም የሮሜ መንግሥት (የቢዛንታይን መንግሥት) አውራጃ ሆነ። ዋና ከተማው ኤደሣ (አሁን ሳንሊዩርፋ፣ ቱርክ አገር) ነበረ። በ600 ዓም የፋርስ መንግሥት ያዘው።

ኦስሮኤኔ
ኦስሮኤኔ በ39 ዓክልበ.

የሰሌውቅያ መንግሥት እየወደቀ የኦስሮኤኔ መንግሥት በ140 ዓክልበ. ግድም የመሠረተው ሥርወ መንግስት ነባታያውያን ከተባለው አረባዊ ነገድ ነበር።

በአንዳንድ ታሪክ ዘንድ፣ ንጉሡ 5ኛው አብጋር በ24 ዓም ለኢየሱስ ክርስቶስ በደብዳቤ ይነጋገሩ ነበር። ኢየሱስም «በእጅ ያልተሠራ መልክ» እንደ ላከላቸው ተብሏል (የጄኖቫ ቅዱስ መልክ ይዩ)። ይህ 5ኛው አብጋር ክርስትናን ተቀብሎ ኦስሮኤኔ ያንጊዜ መጀመርያው ክርስቲያን አገር እንደ ሆነ በአፈ ታሪክ ተብሏል። በሌሎች ምንጮች ዘንድ ግን 9ኛው አብጋር በ192 ዓም ክርስትናን የመንግሥት ሃይማኖት መጀመርያ ያደረጉ ነበሩ።

በ108 ዓም የሮሜ መንግሥት አገሩን በጦር ያዘና እስከ 113 ዓም ድረስ «ደንበኛ ግዛት» አደረጉት። በ206 ዓም እንደገና ወደ ሮሜ መንግሥት ተጨመረ፣ የኦስሮኤኔ ነገሥታትም ከዚያ እስከ 234 ዓም ድረስ በስም ብቻ ቀሩ።

Tags:

መስጴጦምያቱርክአረማይክየሮሜ መንግሥትግሪክኛፋርስ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ማይክሮስኮፕወንጌልኒሞንያየሰው ልጅግስተውሳከ ግሥመድኃኒትግራኝ አህመድመንፈስ ቅዱስወግ አጥባቂነትአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭየወታደሮች መዝሙርጫትሜክሲኮጡት አጥቢየኖህ መርከብየውሃ ኡደትጣልያንየማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላትእስራኤልኮልፌ ቀራንዮየቃል ክፍሎችጥላሁን ገሠሠውሻጡንቻፀደይስም (ሰዋስው)የአዲስ አበባ ከንቲባትዊተርላይቤሪያየአፍሪቃ አገሮችፍቼ ጫምባላላ በዓል በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ባሕላዊ ቅርስ ዝርዝር ላይ በዩኔስኮ ተመዘገ26 Marchየጭቃ እሾህቀለምሥነ ሕይወትጂዎሜትሪመጽሐፈ ጥበብበላይ ዘለቀሊጋባወርቅ በሜዳእንቁራሪትጥርኝየአለም ጤና ድርጅትአርሰናል የእግር ኳስ ክለብዘ ሲምፕሶንስወሲባዊ ግንኙነትየባቢሎን ግንብድመትመጽሐፍ ቅዱስተሳቢ እንስሳየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክእሳተ ገሞራዓረፍተ-ነገርወፍገበጣበጒድጓዱ አጠገብ የሆነች ሳምራዊትቀነኒሳ በቀለበ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትማሪኦጨዋታዎችአዳም ረታየቀን መቁጠሪያፋሲል ግምብዴሞክራሲየመስቀል ጦርነቶችአውስትራልያሰሜን ተራራፈንገስየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንኃይሌ ገብረ ሥላሴማርችመስኮብኛ🡆 More