አንጎል የማዕከላዊ ስርዓተ ነርቭ ክፍል ሲሆን የሚገኘውም በራስ ቅል አጥንት ውስጥ ነው። በራስ ቅል መሸፈኑ በምንም ዓይነት የመታየት የመነካት የመሸተት አልያም የመቀመስ እድል እንዳይኖረው አድርጎታል። ይህ መዋቅር የሚገኘው በዋናነት የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳት ላይ ሲሆን በአብዛሀኛዎቹ የጀርባ አጥንት የሌላቸው እንስሳት ላይም ይገኛል። በአንዳንድ እንደ ኮከብ ዓሳ ያሉ የዓሳ ዝርያዎች ላይ ይህ አካል የሌለ ሲሆን እንደ ስፖንጅ (Sponges) ዓይነት እንስሳቶች ደግሞ ጭራሹንም የስርዓተ ነርቭ መዋቅር የላቸውም።
ከሳይንስ አንጻር አእምሮና አንጎል ይገናኛሉ ተብለው ሲታመን ለዚህ እንደ ዋና ማስረጃ ሆኖ የሚቀርበው በተጨባጩ የአንጎል ክፍሎች ላይ የሚደርስ ጉዳት በአእምሮ (አስተሳሰብ) ላይ የሚያመጣው ለውጥ ነው። ሌላው ተጠቃሽ መረጃ አንድ አንድ መድሃኒቶች በአእምሮ ላይ የሚያመጡት ለውጦች ናቸው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article አንጎል, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.