ግራኝ አህመድ: ኢማም አሕመድ

በተለምዶው ግራኝ አሕመድ ተብሎ የሚታወቀው የጦር መሪ ሙሉ ስሙ ኢማም አሕመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ ሲኾን የኖረውም ከ1507 እስክ ታህሳስ 21፣ 1543 (እ.ኤ.አ) ነበር። ) በዘመኑ በእስልምና ሃይማኖት የኢማምነት ደረጃ የደረሰ ሲኾን የአዳል ግዛት ተብሎ ይታወቅ የነበረውን የጥንቱን የኢትዮጵያ ክፍል በመምራት እንዲሁም በዘመኑ የነበሩትን ነገሥታት ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንዲያፈገፍጉ በማድረግ በታሪክ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ 3/4ኛ የሚኾነውን የኢትዮጵያ ክፍል ለተወሰነ ጊዜ መቆጣጠር ችሏል። አንድ አንድ የታሪክ ተመራማሪዎችም የግራኝ አሕመድ ሰራዊት ከሞላ ጎደል በሱማሌ ጎሳ ሰዎች የተድሎችን በመቀዳጀቱ ምክኒያት በዚህ ስያሜ እንደጠሩት ይነገራል። ይህ መሪ ከ1529 እስከ 1543 ከነበሩት የመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነገስታት ጋር ጦርነት እንዳረገ ታሪክ ይዘግባል።

የኢማም አሕመድ ጎሳ

d͡ʑ ጻሃፊዎች ዘንድ እንደሚታመነው ግራኝ አረብ እንደነበር ሲሆን በሌሎች ታሪክ ተመራማሪወች ዘንድ ግን ሱማሌ እንደሆነ ነው። እንደ እስራኤላዊው የታሪክ ተመራማሪ ሃጋይ ኽልሪች ግን ግራኝ አህመድ ሱማሊኛ ቋንቋን እንደማይናገር አትቷል። በሌላ ሁኔታ ብዙ የታሪክ ጸሃፍት እና መረጃዎች ግራኝ አህመድ የሐረር ተወላጅ መሆኑን ጠቅሰዋል::

ለግራኝ አህመድ እንቅስቃሴ አስተዋጾ ያደረጉ ነገዶች እንደ ኢሳቅ፣ ዳሩድ እና ማረሃን የተሰኙት የሱማሌ ጎሳወች ሲሆኑ ጎሳወቹ ግን በዘር ምክንያት ሳይሆን ያብሩ የነበሩት በሃይማኖት ተመሳሳይነት ነበር።

የኢማሙ ዳግም ድል

በኖራ ሀመድ ሁመድ ✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳ የኢማሙን በ18 ዓመት እድሜ የተገኘ ድል ሰምቶና ደንግጦ መናገሻ ከተማውን ሀረርን ጥሎ ወደ ሶማሊያ የሸሸው ሱልጣን አቡበክር ኪዳር (ኪዳድ) በምትባል ቦታ ተደበቀ።

ኢማሙም በነካ እጁ በሙስሊሙ መካከል ፈሳድ እንዲስፋፋና ሙስሊሙ የአንድነት ሀይልና ወኔው እንዲነጥፍ ምክነያት የሆነውን ሱልጣን አቡበክር ለማጥቃት ወደተደበቀበት ከተማ ተጓዘ። ኢማሙ ቦታው ላይ ሲደርሱም ሱልጣኑ ጦሩን አሰልፎ ጠበቃቸው። ሁለቱ ጦሮችም ዝሁር ወቅት ላይ ተገናኙ ኢማሙና ጓዶቻቸውም በኢስላማዊ ህብረትና ሙሐመዳዊ ወኔ ማጥቃት ጀመሩ። በርካታው የሱልጣኑ ሰራዊት ተገደለ። ከፊሉም ሱልጣኑን ጨምሮ ሸሸ።

ኢማሙ 20 አመት ሳይሞላቸው ሁለተኛውን ጦርነታቸውን በፍፁም ድል አድራጊነት ተወጡ። የሱልጣኑን መሸሸጊያ አወደሙ። በዚህ ጦርነትም ኢማሙ 30 ፈረስና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማረኩ። ነገር ግን ኢማሙ ሐረር ገብተው ብዙ ሳይቆዩ ሱልጣኑ ለቁጥር የሚያዳግት ሰራዊት እዛው ሶማሌያ ላይ ሰበሰበና ኢማሙን ለማጥቃት ወደ ሐረር ተመመ።

የሱልጣኑ ጦር በርካታ ፈረሰኞችን ያካተተ ስለነበር ኢማሙ የሱልጣኑን መቃረብ ሲሰሙ ስልታዊ ማፈግፈግን መረጡ። ከነጦራቸውም ወደ ሁበት ተጉዘው ጋረሙለታ ተራራ ላይ መሸጉ። ሱልጣኑም ሐረር ገባ።

ኢማም አሕመድ በጋሪሙለታ ተራራ ላይ መስፈራቸውን የሰማው ሱልጣን ጦሩን ይዞ ሁበት ገባ። ተራራውንም ለቁጥር ባዳገተው ሰራዊት አስከበበው። ከፍተኛ ጥበቃም አደረገ። የኢማሙ ጦር ከተራራው መውረድና ለህይወት መሠረታዊ የሆኑትን ምግብና የመጠጥ ውሀ ማግኘት አልቻሉም። ሱልጣኑ በዚህ ሁኔታ ለሁለት ሳምንታት ያህል ከበባውን አጠናክሮ ቀጠለ። በስተመጨረሻ ግን የኢማሙ ጦር ተዳከመና ተስፋ መቁረጥ ታየ። ስለሆነም በለሊት የኢማሙ ጦር ወርዶ ከሱልጣኑ ጋር ጦርነት ገጠሙ። ዳሩ ግን የኢማሙ ጦር ለ2 ሳምንት ታግቶ የቆየ በመሆኑ ውጊያው ላይ ቀልጣፋ መሆን አልቻለም። በመሆኑም የኢማሙ ጦር በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃ።

ከአንጋፋ የኢማሙ የጦር አዝማቾች መካከል አንዱ ዑመረዲንም ተገደለ። ኢማሙና ጥቂት ጓዶቻቸው ግን አመለጡ። የኋላ ኋላ ግን በዘመኑ ዑለማኦች ከፍተኛ ጥረት በሁለቱ አሚሮች መካከል ስምምነት እንዲኖር ተደረገ። ስምምነቱም ሱልጣኑ ሸሪዓን ሊጠብቅና በፍትህ ሊያስተዳድር ኢማሙና ጦራቸው ደግሞ መሸፈቱን አቁሞ ለሱልጣኑ ታዛዥ ሆኖ በሰላም እንዲኖር የሚያግባባ ነበር። ስምምነቱም መተግበር ተጀመረ። ኢማሙም ጥማታቸው የስልጣን ሳይሆን የሸሪዓ መጠበቅ መሆኑን ሰጥ ለጥ ብለው ለሱልጣኑ በመታዘዝ አሳዩ። በኋላ ግን ሱልጣኑ ስምምነቱን አፈረሰ።

ቀደምት ዓመታት

ኢማም ግራኝ አህመድ የተወለደው ዘይላ ተብላ ትታወቅ በነበረው የባህር በር አካባቢ በሰሜናዊ ምዕራብ አዳል ( በአሁኑ ዘመን ሶማሊያ) ነበር።

ግራኝ አህመድ: የኢማም አሕመድ ጎሳ, የኢማሙ ዳግም ድል, ቀደምት ዓመታት 
የአዳል ሱልጣኔት

ይህ ታሪካዊ አዳል (ሶማሊያ) የእስልምና ሃይማኖትን የሚከተል መንግስት ይሁን እንጂ በጊዜ ለነበረ የክርስትና ተከታይ ኢትዮጵያው መካከለኛ መንግስት ግብር ይከፍል ነበር። ግራኝም በጎለመሰ ጊዜ ማህፉዝ የተባለን የዘይላ አስተዳዳሪን ልጅ ባቲ ድል ወምበሬ አገባ።.

ነገር ግን ማህፉዝ ከመካከለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ተጣልቶ በአጼ ልብነ ድንግል ላይ ጥቃት አድርሶ ሲመለስ በ1517 ተገደለ። በአዳል እርስ በርስ ጦርነት ተነሳ። ግራኝ አህመድም ከተወሰኑ የትግል ዓመታት በኋላ በስልጣን የሚሻኮቱትን በማሸነፍ ሐረርን ተቆጣጠረ። በዚህ ጊዜ የአዳል መሪ ሆነ።

ዘመቻዎች

በ1527፣ የአዳል መሪ ከሆነ በኋላ፣ ከአዳል ከትሞች የሚጠበቀውን ግብር ለመካከለኛው የኢትዮጵያ መንገስት እንዳይከፈል አገደ። አጼ ልብነ ድንግልም የባሌ ጦር አዛዡን ደግላን ግብሩን እንዲያስከፍል ላከ። ደግላን ግን በአዲር ጦርነት ተሸነፈ። ከዚህ ቀጥሎ ግራኝ ወደ ምስራቅ በመዝመት ሱማሌውችን በጦርነት ግዛቱ አደረገ። ቀስ ብሎም ወደ ምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ብዙ ዘመቻወችን በማካሄድ ስፍር ቁጥር የሌላችቸው ባሪያወችን በመፈንገል በደቡብ አረቢያ፣ ለዘቢድ አስተዳዳሪ በስጦታ መልክ በመላክ በተራው የብዙ ጠመንጃወች ባለቤት ሆነ። በ1528 የልብነ ድንግል ሠራዊት በአዳል ላይ ጥቃት ስላደረሰ፣ ይህን ለመበቀል በ1529 በክርስትያኑ ንጉስ ላይ ኢማም አህመድ ዘመቻውን የኢትዮጵያና አዳል ጦርነት ጀመረ። መሰረታዊው የኢማም አህመድ አላማ ግን "ጅሃድ" ወይም "በሃይማኖት መታገል" ነበር ። በዚህ ጊዜ የአጼ ልብነ ድንግልን ሠራዊት መምጣት የሰሙት የግራኝ ወታደሮች በፍርሃት ተውጠው ለመሸሽ ሲሞክሩ፣ ግራኝ ግን በጽናትና ቆራጥነት አብዛኞቹ ባሉበት እንዲቆሙ በማድረግ የልብነ ድንግልን ሰራዊት ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ደቡብ ምስራቅ በምትገኘው በሽምብራ ቁሬ ጦርነት መጋቢት 1529 አሸነፈ ።



ጦርነቱን ያሸንፍ እንጂ ብዙ ወታደሮች ስላለቁበት ቀሪው ሰራዊቱ ወደሃገሩ ተመልሶ ከንደገና መታገል ሰጋ። በዚህ መሃል ከአረብ አገር 70 ሙሉ ትጥቅ ያላቸው ወታደሮችና ብዙ ጠብመንጃወች እና 7 መድፎች ከኦቶማን ቱርኮች አገኘ። በ1531፣ የግራኝ ጦር የልብነ ድንግልን ሰራዊት አምባሰል አንጾኪያ ላይ ገጥሞ እንደገና ድል አደረገ። ለዚህ ድል መሰረቱ በዕርዳታ ያገኘው መድፍ እንደነበር ሉዶልፍ ሲያትት ከግራኝ ወገን የተተኮሰ መድፍ ጥይት በአጋጣሚ ልብነ ድንግል ሰራዊት መካከል ወደቀ፣ ይህ እንግዳ መሳሪያ የሚያሰክትለውን ቁስል እንኳ እንዴት ማዳን እንደሚቻል የማያውቁጥ ኢትዮጵያውያን በድንጋጤ ተበታተኑ ። ከዚህ በኋላ የኢማሙ ሰራዊት ወደሰሜን በመዝመት በሃይቅ፣ ወሎ ደሴቶች ላይ የነበሩትን አካባቢዎችን ተቆጣጠረ። ቀጥሎም ትግራይ ውስጥ ይጠብቀው የነበረውን ሰራዊት በማሸነፍ አክሱም ከተማ ተቆጣጠረ።

ይህ ከመሆኑ በፊት አስቀድማ ንግስት እሌኒ የተባለችው የሃድያ ንግስት ( የዘርዓ ያዕቆብ ሚስት)፣ ለፖርቱጋሎች የወታደር እርዳታ እንዲያረጉ መልዕክት ልካ ኖሮ፣ ታህሳስ 10፣ 1541 400 ጠመንጃ ያነገቱ የፕርቱጋል ሰራዊት ምጽዋ ላይ አረፉ። በዚህ ጊዜ አጼ ልብነ ድንግል በስደት እያለ በ1540 ሲሞት እሱን ተክቶ አጼ ገላውዲወስ ንጉሰ ነገስት ሆኖ ነበር። በ ክሪስታቮ ደጋማ የሚመራው የፖርቹጋሎቹ ሰራዊትና ኢትዮጵያውያን ሚያዚያ 1፣ 1542 በጃርቴ ጦርነት (ጃርቴ በሌላ ስሙ አናሳ ሲባል በአምባላጌ እና በአሻንጌ ሃይቅ መካከል የሚገኝ ቦታ ነው) ከ ግራኝ ሰራዊት ጋር የመጀምሪያ ፍልሚያ አደረገ። በዚህ ጊዜ ፖርቱጋሎቹ ግራኝን ለመጀመሪያ ጊዜ ማየታቸው ሲሆን በጊዜው የነበረው ፖርቹጋላዊው ካስታንሶ ክሩቅ ሆኖ ስላየው ስለግራኝ እንዲህ ይላል፦

    በሱ በኩል ያለውን የጦር አውድማ በሚዘጋጅበት ጊዜ፣ የዘይላው ንጉስ ኢማም አህመድ ኮረብታው ላይ ወጣ። በዚህ ጊዜ ብዙ ፈረሰኞች አብረው ተከትለውት ነበር፣ እግረኞችም እንዲሁ። የእኛን የጦር ቀጠና ለመመርመር፣ እኮረብታው ጫፍ ሲደረስ ከ300 ፈረሶች እና ሶስት ግዙፍ ባንዲራወች ጋር ቆመ። አርማዎቹም ሁለቱ ነጭና መካከላቸው ላይ ቀይ ጨረቃ ምልክት ሲኖራቸው አንዱ ደግሞ ቀይና መሃሉ ላይ ነጭ ጨረቃ ያሉባቸው ከንጉሱ ዘንድ ምንጊዜም የማይለዩ ነበሩ ይላል።

በዚህ ሁኔታ ለ4 ቀናት በመፋጠጥና መልዕክት በመለዋወጥ እኒህ የማይተዋወቁ ሁለት ሰራዊት ጊዜያቸውን ካሳለፉ በኋላ ክሪስታቮ ደጋማ እግረኛ ወታደሮቹን (ኢትዮጵያኖችንም ይጨምራል) በአራት ማዕዘን ቅርጽ በማደራጀት ወደ ኢማሙ ሰራዊት ዘመተ። የእስላሙ ሰራዊት፣ ብዙ ጊዜ እየደጋገመ ጥቃት ቢያደረስም በመድፍና በጠመንጃ የታጠረ አራት ማዕዘኑ ሊሸነፍ አልቻለም። በዚህ ጦርነት መካከል በድንገት በተተኮሰ ጥይት ግራኝ አህመድ እግሩ ላይ ቆሰለ። ስለሆነም የኢማሙ ሰራዊት መሸሽ መጀመሩን ያዩት የኢትዮጵያና የፖርቹጋል ሰራዊት ተበታትኖ የሚሮጠውን ሰራዊት በማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ። ይሁንና የቀሩት ወታደሮች ከእንደገና በማደራጀት ኢማሙ ጦርነት ከተካሄደብት ወንዝ ራቅ ብሎ ሰፈረ።

በሚቀጥሉት ጥቂት የግራኙ ጎራ አዳዲስ ወታደሮች በማስመጣት በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከር ጀመረ። ይህ ነገር ያላማረው ደጋማ ቶሎ ብሎ ጦርነት መግጠም አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ መጋቢት 16 ላይ አሁንም አራት ማዕዘን በመስራት ዘመተ። ምንም እንኳ የኢማሙ ጦር ከበፊቱ በበለጠ ቁርጠኝነት ቢዋጉም፣ በድንገት በፈነዳ የጥይት ቀልህ ምክንያት ፈረሶቹ በመደናገጣቸው አራቱ ማዕዘን አሁንም አሸነፈ። በዚህ ጊዜ የኢማሙ ሰራዊት በዕውር ደንብስ እያመለጠ ሸሸ። ክሳታንሶ የተባለው ፖርቱጋላዊም በጸጸት እንዲህ ብሎ መዘገበ፡

    መቶ የሚሆኑ ፈረሶች ቢኖሩን ኑሮ የዛሬው ቀን ድል የተሟላ ይሆን ነበረ ምክንያቱም ንጉሱ እራሱ በቃሬዛ አራት ሰወች ተሸክመውት ነው ያመለጠው። ቀሪው ሰራዊትም የሸሸው በተረጋጋ ሁኔታ ሳይሆን በእውር ድንብስ ነበር።

የመረብ ምላሽ (አሁኑ ኤርትራ) አስተዳዳሪ ባህር ንጉስ ይስሃቅ ከተደባለቀ በኋላ፣ አጠቃላዩ ሰራዊ ወደ ደቡብ በመነቀሳቀስ በ10ኛው ቀን ከግራኙ ጦር ፊት ለፊት አረፈ። በዚህ መሃል ክረምት ስለገባ በዝናቡ ምክንያት ደጋማ ለሶስተኛ ጊዜ ግራኝን ሊገጥመው ፈልጎ ግን ሳይችል ቀረ። በንግስት ሰብለ ወንጌል ጎትጓችነት ደጋማ በወፍላ፣ ከአሻንጌ ሃይቅ ፊት ለፊት፣ ከግራኝ ጦር ብዙም ሳይርቅ ክረምቱን አሳለፈ። በዚህ ትይዩ ኢማሙ ደግሞ በ ዞብል ተራራወች ላይ ሰራዊቱን አስፈረ።

ድል በጦር መሳሪያ ብዛት እንደሚወሰን የተገነዘበው ግራኝ ለእስላሙ አለም የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ። አረቦችም 2000 ጠመንጃወችና መድፎች እንዲሁም ከቱርክ 900 የተመረጡ ወታደሮች ተላኩለት። ባንጻሩ የፖርቹጋሎቹ ወታደሮች ብዛት በተለያዩ ግዴታወችና በጦርነት ላይ በደረሰው ሞት ምክንያት ከ400 ወደ 300 ዝቅ ብሎ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ ክረምት አልፎ በጋ ሲሆን በሃይል የተጠናከረው ግራኝ አህመድ በፖርቹጋሎቹ የጦር ቀጠና ላይ ጥቃት በማድረስ ቁጥራቸውን ወደ 140 አመናመነው። ክርስታቮ ደጋማም ቆስሎ 10 ከሚሆኑ ወታደሮቹ ጋር ተማረከ። በዚህ ጊዜ በሃይማኖቱ ከጸና እንደሚገደል ከሰለመ ግን እንደማይገደል ተነግሮት ሃይማኖቴን አልቀይርም በማለቱ በተማረክበት ተገደለ።

ከዚህ ጥቃት የተረፉትና የአጼ ገላውዲወስ ሰራዊት በመጨረሻ ተገናኝተው ሃይላቸውን በማጠናከር የካቲት 21፣ 1543 የወይና ደጋ ጦርነት ተብሎ በሚታወቀው ጥቃት አደረሱ። በዚህ ጦርነት 8560 የሚሆኑት የኢትዮጵያና ፖርቱጋል ሰራዊት 15,200 የሚሆነውን የኢማሙን ሰራዊት አሸነፈ። ኢማሙ በጥይት ተመትቶ ለማምለጥ ሲሞክር ካልአይ የተባለ ወጣት የፈረሰኛው ጦር መሪ ተከታትሎ ሄዶ አንገቱን ቀልቶ ገደለው።

የግራኝ ሚስት፣ ባቲ ድል ወምበሬም ከተራረፉ የቱርክ ወታደሮች ጋር አምልጣ ሐረር ገባች። ተከታዮቿንም በማስተባበር የባሏን ሞት ለመበቀል የባሏን እህት ልጅ ኑር ኢብን ሙጃሂድን በማግባት ተነሳች። ፈጠገር ውስጥ የኑር ኢብን ሙጃሂድወታደሮች ጋር ሲዋጋ አጼ ገላውዲወስ እንደተገደለ እና አስከሬኑ ተፈልጎ አንገቱ ተቆርጦ ወደ ሐረር እንደተላከ አንዳንድ የታሪክ ጸሓፊያን ይዘግባሉ::

አቤቶ ሀመልማል የተባለው የአፄ ገላውዴዎስ አጎት ልጅ ሰራዊቱን እየመራ ሀረር ከተማ ገብቶ ከተማይቱን ከዘረፈ እና ካወደመ በኋላ ሱልጣን በረከትን ማርኮ አንገቱን ቀልቶ እደገደለውም ተፅፏል።

ማጣቀሻወች

ፉቱሑል ሐበሻ ሺሃቡዲን ኣረብ ፈቂህ

ሷሊሕ አስታጥቄ የፌስ ቡክ ገፅ

<https://www.facebook.com/sualihastatkehussen/>

Tags:

ግራኝ አህመድ የኢማም አሕመድ ጎሳግራኝ አህመድ የኢማሙ ዳግም ድልግራኝ አህመድ ቀደምት ዓመታትግራኝ አህመድ ዘመቻዎችግራኝ አህመድ ማጣቀሻወችግራኝ አህመድ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ቻርሊ ቻፕሊንሐና ወኢያቄምየአፍሪካ ቀንድአብዮትዲያቆንየመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊነትኢንዶኔዥኛፈርዲናንድ ማጄላንባሕር-ዳርእቴጌየሮማ ግዛትዋናው ገጽዋና ከተማኤቨረስት ተራራፑንትይሖዋኦሮሞተመስገን ተካናፖሌዎን ቦናፓርትሽመናቅዱስ ገብርኤልየማቴዎስ ወንጌልአውስትራልያየኮንሶ ባህላዊ የእርከን ስራኢትዮጲያሳክራመንቶደራርቱ ቱሉአምባሰልዝግባድር ቢያብር አንበሳ ያስርእሌኒየኩሽ መንግሥትድግጣአለማየሁደቡብ አሜሪካኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴስምየኢትዮጵያ ንግድ ባንክየልም እዣትጥግየእብድ ውሻ በሽታሪፐብሊክሊያ ከበደእንስሳ2ኛው ዓለማዊ ጦርነትሱርማቡዳየኢትዮጵያ እጽዋትእንግሊዝኛህሊናነብርደብረ ዘይትነፋስ ስልክzlhbzየሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀልቅዱስ ሩፋኤልየአሜሪካ ዶላርአቡጊዳአባ ጉባይኩኖ አምላክኮንጎ ሪፑብሊክዳዊት ጽጌገጠር565 እ.ኤ.አ.ጣና ሐይቅየኢትዮጵያ ሙዚቃቀዳማዊ ዳዊትቻይናተውሳከ ግስ🡆 More