ቢዮንሴ ጊሴሌ ኖውለስ (Beyoncé Giselle Knowles) ሙሉ ስሟ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነት ያላት የአር አንድ ቢ (R and B) የሙዚቃ ዘርፍ አቀንቃኝ፣ የሙዚቃ አዘጋጅ፣ ተዋናይት፣ ሞዴል እና የሙዚቃ ደራሲ ናት። እ.አ.አ.
በሴፕቴምበር 4 1981 ሀውስተን በቴክሳስ ውስጥ ተወለደች። በልጅነቷ ጀምሮ ማቀንቀን ትወድ የነበረችው ይህች አርቲስት ገና በወጣትነት እድሜዋ ዴስትኒስ ቻይልድስ የተሰኘ የሙዚቃ ቡድን ከ ባልደረቦቿ ኬሊ ሮላንድ እና [[ዊሊያምስ ጋር በመሆን እ.አ.አ. በ 1997 ቴክሳስ ውስጥ አቋቋመች (የኋላ ኋላ ግን ቡድኑ ፈርሶ እ.አ.አ ከ2006 ጀምሮ ለብቻዋ መስራት ጀምራለች)። ቡድኑ እስከፈረሰበት አመት ድረስ በተለያዩ ስራዎች ውጠታማ ነበር። በተለይ ከባልተቤቷ ጄዚ ጋር የሰራችው ክሬዚ እን ላቭ የተሰኘው ዜማ ከፍተኛ ዝናን አትርፏል። በ2008 እ.አ.አ ያወጣችው I'm... sasha fierce አልበሟ አሁን ለደረሰችበት ከፍተኛ እውቅና ዋናውን ድርሻ ይይዛል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ቢዮንሴ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.