ድልሙን ወይም ተልሙን በሱመርኛና አካድኛ መዝገቦች የሚጠቀስ አገር ሲሆን በዛሬው ባህሬን አካባቢ እንደ ተገኘ በአብዛኞቹ መምህራን ይታስባል።
ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ በሚባል ትውፊት «የድልሙን አገር ገና ሳይኖር ኡሩክ በደንብ ተመሰረተ» ይለናል።
በኡሩክ በተገኙ ከሁሉ ጥንታዊ ጽላቶች ላይ (2300 ዓክልበ. ግድም)፣ «የድልሙን መጥረቢያ»፣ «የድልሙን ሹም»፣ እና «የድልሙን ሰዎች ሱፍ ድርሻ» ይጠቀሳሉ። በተጨማሪ በዚያ ጊዜ ያህል የገዛው የላጋሽ መጀመርያ አለቃ ኡር-ናንሼ ባጻፈ ጽሑፍ ዘንድ፣ «የድልሙን መርከቦች እንጨት ከውጭ አገር እንደ ቀረጥ አመጡለት»።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ድልሙን, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.