ደ ዱ ዲ ዳ ዴ ድ ዶ ዷ
የአቡጊዳ ታሪክ | |||||
---|---|---|---|---|---|
አ | በ | ገ | ደ | ||
ሀ | ወ | ዘ | ሐ | ጠ | የ |
ከ | ለ | መ | ነ | ሠ | ዐ |
ፈ | ጸ | ቀ | ረ | ሰ | ተ |
ድንት (ወይም ድልት) በአቡጊዳ ተራ አራተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያና በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች አራተኛው ፊደል «ዳሌት» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ዳል» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 4ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 8ኛው ነው።) በግሪክም 4ኛው ፊደል «ዴልታ» ይባላል። በነዚህ ቋንቋዎች ሁሉ አጠራሩ «ድ» ነው።
በአማርኛ ደግሞ «ጀ ጁ ጂ ጃ ጄ ጅ ጆ» ከ«ደ...» ትንሽ ተቀይሯል።
ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል | ቅድመ-ሴማዊ | ሣባ | ግዕዝ | ||
---|---|---|---|---|---|
| ደ |
የድንት መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ ወይም የደጅ ወይም የዓሣ ስዕል መስለ። ለደጅ ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ «ዐእ» ነበር።
ከነዓን | አራማያ | ዕብራይስጥ | ሶርያ | ዓረብኛ |
---|---|---|---|---|
ד | ﺩ |
የከነዓን «ዳሌት» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ዳሌት» የአረብኛም «ዳል» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ደልታ» (Δ δ) አባት ሆነ፤ እሱም የላቲን አልፋቤት (D d) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Д, д) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ድንት» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፬ (አራት) ከግሪኩ Δ በመወሰዱ እሱም የ«ደ» ዘመድ ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ድንት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.