ትሪጎኖሜትሪ

ትሪጎኖሜትሪ የሚለው ቃል ከግሪክ የመጣ ( ትሪጎኖን = ሦሥት ጎን፣ ሜትሪ = መለካት) የሶስት ጎኖችን ማዕዘናትና አቃፊ ጎኖቻቸውን ተዛምዶ የሚያጠና የሒሳብ ክፍል ነው። እኒህ ተዛምዶዎች ብዙ ጊዜ የሚገለጡት በትሪጎኖሜትሪክ ፈንክሽን ሲሆን ጥናቱ በአጠቃላይ ለተደጋጋሚ ክስተቶች ጥናት፣ በተለይ ለሞገዶች ከፍተኛ ጥቅም አለው። ስለሆነም የትሪጎኖሜትሪ ጥናት ሰፊ ለውጥ ያሳየው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3ኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች ጂዎሜትሪን ለሥነ ከዋክብት ጥናት መጠቀም በጀመሩበት ጊዜ ነበር.

። I

ትሪጎኖሜትሪ
በዓለም አቀፍ የጠፈር መናህሪያ ተተክሎ ያለው የሮቦት እጅ እንቅስቃሴው የሚመራው በመገጣጠሚያው ላይ ባሉ ማዕዘናት አማካይነት ነው። ብሮቦቱ እጅ ላይ ያለው ጠፈርተኛ እንቅስቃሴ የሚሰላው የትሪጎኖሜትሪ ስሌቶቾን በማዕዘናቱ ላይ በተደጋጋሚ በመፈጸም ነው

በአሁኑ ወቅት፣ ትሪጎኖሜትሪ ለሒሳብሳይንስቴክኖሎጂሥነ ከዋክብት ጥናትና ለመሬት ጥናት የሚያግለግል ዋና የሒሳብ መሳሪያ ነው።

በአጠቃላይ መልኩ

ትሪጎኖሜትሪ 
በቀጥተኛው ሶስት ጎን: sin A = a/c; cos A = b/c; tan A = a/b.

የአንድ ሶስት ጎን አንድ ማዕዘን 90 ዲግሪ ቢሆንና አንዱ ሌላው ማዕዘን ከታወቀ፣ ቀሪው ሶሰኛ ማዕዘን ምንጊዜም ይታወቃል። ለዚህ ምክንያቱ ማናቸውም ሶስት ጎኖች የውስጥ ማዕዘኖቻቸው ሲደመሩ ሁልጊዜ 180 ስለሚሞሉ ነው፡፡ ማዕዘኖቻቸው ታወቁ ማለት ደግሞ ምንጊዜም የጎኖቻቸው ውድር ቋሚ ነው ማለት ነው።

ስለሆነም የአንድ ቀጥተኛ ሶስት ጎን አንድ ማዕዘን A, እና ጎኖች a, b, c ቢሰጡ፣ የጎኖቹ ውድሮች እንዲህ ሲባሉ በትርጎኖሜትሪ ፈንክሽኖች ይተረጎማሉ:

  • ሳይን(Sine) ከማዕዘኑ ትይዩ ያለው ጎን ለተጋዳሚው(hypotenuse) ጎን ሲካፈል
      ትሪጎኖሜትሪ 
  • ኮሳይን(Cosine) ፈንክሽን (cos), ለማዕዘኑ ታካኪ የሆነው ጎን ለተጋዳሚው ጎን ሲካፈል
      ትሪጎኖሜትሪ 
  • ታንጀንት(Tangent) ለማዕዘኑ ትይዩ የሆነው ጎን ለታካኪው ሲካፈል
      ትሪጎኖሜትሪ 

የኒህ ፈንክሽኖች ብዜታዊ ግልባጮች፣ ተራ በተራ ፣ ኮሴካንት ('cosecant) (csc ወይንም cosec), ሴካን (secant) (sec), እና ኮታንጀንት (cotangent) (cot), በመባል ያወቃሉ።

ከላይ የተጠቀሱት ፈንክሽኖች፣ ከተሰጠ ማዕዘን ተነስተው ውድር የሚያገኙ ሲሆን፣ ከተሰጠ ውድር ተነስተው ማዕዘኑን ማስገኘት የሚያስችሉ ዘዋሪ ፈንክሽኖችም አሉ። እኒህም አርክሳይን(arcsine), አርክኮሳይን(arccosine), እና አርክታንጀንት(arctangent) በመባል ይታወቃሉ። ,

እላይ የተጠቀሱትን ፈንክሽኖች በመጠቀም ማናቸውም በሶስት ጎን ላይ የሚነሱ የማዕዘን ጥያቄወችን መመለስ ይቻላል። ሁለት ጎናቸው የሚያቅፉት ማዕዘን፣ ወይም፣ ሁለት ማዕዘኖቻቸው እና አንድ ጎናቸው፣ ወይንም ሶስቱ ጎናቸው የሚታወቅ ሶስት ጎኖች፣ ሌሎች ቀሪ ያልታወቁ ጎኖቻቸውና ማዕዘኖቻቸው በትርጊጎኖሜትሪ እንዲታወቅ ያችላል።

ለምሳሌ አንድ ፎቅ የሚያጠላው ጥላ ርዝመትና የጥላው ማዕዘን ቢታወቅ፣ የፎቁ ርዝመት በትሪጎኖሜትሪ ተሰልቶ ሊገኝ ይችላል።

የትሪጎኖሜትሪ ህጎች በማናቸውም የጂዎሜትሪ ክፍሎች ተጠቃሚነት ያገኛሉ። ለዚህ ምክንያቱ ማናቸውም የጂዎሜትሪ ምስሎች ከተወሰኑ ሶስት ጎኖች ቅንጅት የሚመጡ ናቸውና።


የትሪጎኖሜትሪ ህግጋት

መሰረታዊ እኩያዎች

እኒህ እኩልዮሾች ለማናቸውም ማዕዘናት ያገለግላሉ

    ትሪጎኖሜትሪ 
    ትሪጎኖሜትሪ 
    ትሪጎኖሜትሪ 

ምዕዘናት ማሻገሪያ ቀመሮች

    ትሪጎኖሜትሪ 
    ትሪጎኖሜትሪ 
    ትሪጎኖሜትሪ 
    ትሪጎኖሜትሪ 

ተጨማሪ ቀመሮች

ትሪጎኖሜትሪ 
a,b,c የሶስት ጎኑ ጎኖች ሲሆኑ A,B,C ደግሞ ከጎኖቹ ትይዩ የሚገኙ ማዕዘናት ናቸው

በሚከተሉት እኩልዮሾች A, B እና C የሶስት ጎን ማዕዘና ሲሆኑ a, b እና c ደግሞ ከማዕዘናቱ ፊት ለፊት የሚገኙ ጎኖች ናቸው

የሳይኖች ህግ

የሳይኖች ህግ እንዲህ ይጻአል

    ትሪጎኖሜትሪ 

R እዚህ ላይ በሶስት ጎኖቹ ሶስት ነጥቦች ላይ የሚሳልን ክብ ራዲየስ ይወክላል ፡

    ትሪጎኖሜትሪ 

የሶስት ጎኑ ስፋት ደግሞ እንዲህ ይሰአላል:

    ትሪጎኖሜትሪ 

የኮሳይኖች ህግ

የኮሳይኖች ህግ፣ የፓይታጎሪያን እርግጥ ከቀጥተኛ ሶስት ጎን ወደ ለማንኛውም ሶስት ጎን ጥቅም ሲሻገር የሚይዘው ቅርጽ ነው፦

    ትሪጎኖሜትሪ 

ወይም ደግሞ፦

    ትሪጎኖሜትሪ 

የታንጀንቶች ህግ

የታንጀንቶች ህግ እንዲህ ይላል:

    ትሪጎኖሜትሪ 

የኦይለር ቀመር

የኦይለር ቀመር, በሓሳቢው ኦይለር የተደረሰበት ቀመር ሲሆን፣ እንዲህ ይላል ትሪጎኖሜትሪ ፣ ሲተነተን የሚከተሉትን ቀመሮችና ትርጓሜዎች ይሰጣል፦

    ትሪጎኖሜትሪ 

ማጣቀሻዎች

የውጭ ማያያሻዎች (እንግሊዝኛ)

Tags:

ትሪጎኖሜትሪ በአጠቃላይ መልኩትሪጎኖሜትሪ የ ህግጋትትሪጎኖሜትሪ ተጨማሪ ቀመሮችትሪጎኖሜትሪ ማጣቀሻዎችትሪጎኖሜትሪ የውጭ ማያያሻዎች (እንግሊዝኛ)ትሪጎኖሜትሪሞገድሥነ ከዋክብትሶስት ጎን

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

እምስባርነትኮልካታየኩሽ መንግሥትቶማስ ኤዲሶንጫትገንዘብአውሮፓወርቅ በሜዳውሻ አይበላሽ ጥልወረቀትሰሜን ተራራፕዌርቶ ሪኮዘረኝነት በሩሶ-ዩክሬንያን ጦርነትእየሱስ ክርስቶስየቃል ክፍሎችጂጂአርጎብኛየኢትዮጵያ ነገሥታትፈረስ ቤትገብስንጉሥየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንየኢትዮጵያ ሶማሊያ ጦርነትደቂቅ ዘአካላትግራኝ አህመድእስፓንኛብሉይ ኪዳንመጠይቃዊ ዓረፍተ-ነገርአሕጉርአብርሀም ሊንከንየሥነ፡ልቡና ትምህርትአርሰናል የእግር ኳስ ክለብሕንድ ውቅያኖስቁንዶ በርበሬሜክሲኮትዝታጥሩነሽ ዲባባቀዳማዊ ዓፄ ዮሐንስመካከለኛ ዘመንግዕዝየማርያም ቅዳሴሰንኮፉ አልወጣምስም (ሰዋስው)ሽፈራውጨረቃመነን አስፋውየአፍሪቃ አንድነት ድርጅትየአገሮች ገንዘብ ምንዛሪአስቴር አወቀእሸቱ መለስየሠገራ ትቦ ንጣፍ መድማት ወይመ መቁስል (ሄሞሮይድ)ፍቅር እስከ መቃብርሊጋባዝግመተ ለውጥቻይንኛመንግስቱ ኃይለ ማርያምዕዝራጡት አጥቢየተባበሩት የሀገር ንጉሳዊ አገዛዝካራማራጋሞአዶልፍ ሂትለርሰባትቤትAየአሜሪካ ብሔራዊ ጦርነትየአዋሽ በሔራዊ ፓርክአቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞቅንጭብየጊዛ ታላቅ ፒራሚድቆስጣቡና🡆 More