መቐለ (አማርኛ፦ መቀሌ) የትግራይ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከአዲስ አበባ 783 ኪ.ሜ.
ወደ ሰሜን ትገኛለች። ከ300,000 አስከ 350,000 የሚገመት የሕዝብ ብዛት ስላላት ከሰሜን ኢትዮጵያ ትልቋ ከተማ ያደርጋታል። መቐለ ለ አጼ ዮሐንስ ፬ኛ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን በ19ኛው ክፈለ ዘመን ነው የተመሠረተችው። መቐለ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች በንግድና ትምህርታዊ ማዕከላዊነትዋ ትታወቃለች። በታላቁ አፍሪካዊ ጄነራል ራስ አሉላ አባ ነጋ የተሰየመ ዓለም አቀፋዊ አየረ ማረፊያ አላት። በተጨማሪም እንደነ መስፍን ኢንዱስትርያል፣ መሰቦ ሲሚንቶ፤ ሌሎች ፋብሪካዎችና መቐለ ዩኒቨርሲቲ የመሳሰሉ ትላልቅ ተቋማት በከተማዋ ይገኛሉ።
መቐለ | |
ከተማ | |
ሓኽፈን ጎዳና (መቐለ) | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | ትግራይ ክልል |
ዞን | መቐለ ልዩ ዞን |
ከፍታ | 2,084 ሜ. |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 169,207 |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article መቀሌ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.