ጋፋት በደቡብ ጎንደር ከደብረ ታቦር ትንሽ ወጣ ብላ የምትገኝ ቦታ ናት። በዚች ቦታ ከጥንት ጀምሮ አንጥረኞችና የእጅ ጥበብ አዋቂወች ይኖሩበት እንደነበር ትውፊት አለ። ሆኖም ግን በታሪክ ትልቅ ቦታን ያገኘቸው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ዓፄ ቴዎድሮስ የሴባስቶፖል መድፍን የአውሮጳ ሚስዮናውያን የአካባቢውን አንጥረኞችንና ቀጥቃጮችን በማሰለፍ በዚህ ቦታ አስርተው በማስመረቃቸው ነው። ከሴባስቶፕል በተጨማሪ 8 ሌሎች መድፎች ተሰርተው እንደነበር እና ላያቸው በአማርኛ በተጻፉ ጥቅሶች ያጌጡ እንደነበር ሚሲዮኑ ቴዎፍሎስ ዋልድማየር መዝግቧል።
ይህ ቦታ የዚያን ዘመኑን የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ቅሪቶች ብዙ የሉትም። ምክንያቱም ንጉሱ ወደ መቅደላ ሲሄዱ ከተማውን አቃጥለውት ነበርና።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጋፋት, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.