ጉን በቻይና አፈ ታሪክ ከኋሥያ ንጉሥ ያው መኳንንት አንዱ ነበር። ከዚህ ቀድሞ በኋሥያ የነገሠው ዧንሡ የጉን ቅድመ-አያት መሆኑ ይባላል። ያው የቾንግ አገረ ገዥ አደረገው፤ ይህም ቦታ ደብረ ሶንግ እንደ ሆነ ይታመናል። በያው ዘመን የቻይና ታላቅ ጎርፍ በወንዞቹ ጀመረ። ስለዚህ ያው ጉንን ልዩ ሚኒስትር እንዲሆን ሾመው። ግድብ በመሥራት ወንዞቹን እንዲያስተዳድራቸው አዘዘው። ትውፊቶች እንድሚሉ፣ ግድብ ለመሥራት ልዩ ተዓምራዊ የአፈር አይነት «ሺራንግ» («ሕያው አፈር») ጠቀመው። ሆኖም ጉን ለ፱ ዓመታት ይህን ሞክሮ ጎርፎቹ እንደገና ግድቦቹን ሰበሩ፣ ብዙ መንደረኞች ተሰመጡ። ስለዚህ ያው ጉንን ሻረውና በፈንታው አማቹን ሹንን ሾመው። ከዚህ ጥቂት ጊዜ በኋላ ያው ዙፋኑን ትቶ ሹንንም አልጋ ወራሽ አድርጎት ያን ጊዜ ሹን የኋሥያ ንጉሥ ሆነ። ጉን ግን ወደ ዩሻን («የላባ ጠራራ») በስደት ሄደ። ሆኖም የጉን ልጅ ዩ ከዚህ በኋላ ጎርፎቹን በሺራንግ በመገድብ ተከናወነ፣ እርሱም የሹን ተከታይ ሆኖ «ዳ ዩ» («ታላቁ ዩ») ተብሎ የሥያ ስርወ መንግሥት የመሠረተ ነው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ጉን, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.