አካድ (ሱመርኛ፡ አጋደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ፡ አርካድ) በመስጴጦምያ የተገኘ ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ቦታው በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ከሲፓርና ከኪሽ መካከል እንደ ነበር ቢታሠብም ፍርስራሹ ግን እስካሁን ድረስ አልተገኘም። ዙሪያው በሱመርኛ 'ኡሪ-ኪ' ወይም 'ኪ-ኡሪ' ተባለ።
በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር መሠረት አካድ (አጋደ) የገነባው ታላቁ ሳርጎን ነበረ። ሆኖም ከተማው ከሳርጎን ቀድሞ በኡሩክ ንጉሦች ኤንሻኩሻና እና ሉጋል-ዛገሢ ዘመናት እንደተገኘ ከጽሕፈቶች ይታወቃል። በመጽሐፍ ቅዱስም (ዘፍ. 10፡10) ዘንድ ናምሩድ ከሠሩት ከተሞች 1ዱ መሆኑ ይቆጠራል። ከዚህ በላይ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ሱመራዊ አፈ ታሪክ፣ ልሣናት የተደባለቁባቸው አገሮች ሹባር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙሪያ) እና የማርቱ አገር በመባላቸው፤ ይህም የአካድን ጥንታዊነት ይመሰክራል። እንደገና በብዙ ጥንታዊ መዝገቦች፣ ከሰናዖር (ሱመር) ዙሪያ ሌሎቹ '4 ሩቦች' ሲዘረዘሩ እነርሱ 'ማርቱ' (አሞራውያን)፣ 'ሹባር' (አሦር?)፣ ኤላምና 'ኡሪ-ኪ' (አካድ) ናቸው።
ከአካድ ንጉሥ ከሳርጎን ዘመን ጀምሮ የአካዳዊ መንግሥት ዋና ከተማ ሆኖ ከ2077 እስከ 2010 ዓክልበ. ገደማ ገዛ። አካድኛ አንድ ሴማዊ ቋንቋ ነበርና ይህ ቋንቋ በአካዳዊ መንግሥት ጊዜ በመስጴጦምያም ሆነ በኤላም ይፋዊ ሆነ።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article አካድ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.