ኅዳር ፲፫

ኅዳር ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፫ተኛው እና የመፀው ወቅት ፵፰ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፪ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፱፻፲፭ ዓ/ም - የብሪታንያ ተወላጁ የሥነ ቅርስ ባለሙያ ሃዋርድ ካርተር የጥንታዊ ግብጽ ንጉሥ ቱታንኻሙንን ቤተ መቃብር ከፈተ።
  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በቅርብ ነፃነቷን ክተቀዳጀችው የናይጄሪያ መንግሥት ጋር የአምባሳዶር ሏጥ እንደሚያደርጉ ይፋ አደረገ።
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በዳላስቴክሳስ ሠላሳ አምሥተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጠመንጃ ጥይት ተገድለው ሞቱ። በሚጓዙበት ተሽከርካሪ ውስጥ አብረዋቸው የነበሩትም የቴክሳስ ገዥ ጆን ኮናሊ በጥይት ተመተው ቆስለው ነበር። በዚህም ታሪካዊ ድርጊት የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ ተይዞ በቁጥጥር ሥር ሆነ። የዚያኑ ዕለት ምክትል ፕሬዚደንቱ ሊንደን ቢ ጆንሰን ሠላሳ ስድስተኛው ፕሬዚደንት ሆነው የመሀላ ሥርዐታቸውን በመፈጸም ስልጣኑን ተቀበሉ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው የማዕድን ሚኒስትር አቶ ተሾመ ገብረ ማርያም በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) ታሰሩ።
  • ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - በእስፓኝ አምባ ገነኑ ፕሬዚደንት ፍራንሲስኮ ፍራንኮ በሞቱ በሁለተኛው ቀን ቀዳማዊ ሁዋን ካርሎስ የአገሪቷ ንጉሥ ተባሉ።
  • ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - በናይጄሪያ በወቅቱ ሊካሄድ በታቀደው ከ”ወይዘሪት ዓለም” የቁንጅና ውድድር ጋር በተያያዘ ጉርምርምታ መነሻነት “ThisDay” በተባለ የናይጄሪያ ጋዜጣ ላይ የወጣው ‘ሐይማኖት ነክ’ አንቀጽ ባስከተለው ሽብር ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ውድድሩም በዚሁ ሽብር ምክንያት ወደ ለንደን ተዛወረ።
  • ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - በዩክራይን የተካሄደውን የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሕዝቡ ትልቅ ጭብርብርነት ተፈጽሟል በሚል መነሻነት፣ በብዙ አሥራት ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ የዕጩዋቸውን፣ የቪክቶር ዩሽቼንኮን ስም እየጠሩ የኪዬቭን ከተማ አጥለቀለቋት። ይሄውም የተቃውሞ ሰልፍ “የብርቱካን አብዮት” (Orange Revolution) ተብሎ የተሰየመውን ቅስቀሳ የተጀመረበት ዕለት ነው።

ልደት

  • ፲፰፻፩ ዓ/ም - እስከዛሬ በስሙ የሚጠራውን የጉዞ ወኪል የመሠረተው የብሪታንያ ተወላጅ ቶማስ ኩክ

ዕለተ ሞት

  • ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በተለይም ሄልሲንኪ ላይ በ፲፱፻፵፭ በተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር በአምሥት እና በአሥር ኪሎሜትር እንዲሁም በማራቶን የሩጫ ውድድሮች አሸናፊነቱ ስመ ጥሩነትን ያተረፈው የቼክ አትሌት ኤሚል ዛቶፔክ (“የቼኩ ባቡር”)

ዋቢ ምንጮች

  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
  • {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974

Tags:

ኅዳር ፲፫ ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎችኅዳር ፲፫ ልደትኅዳር ፲፫ ዕለተ ሞትኅዳር ፲፫ ዋቢ ምንጮችኅዳር ፲፫ሉቃስመፀውማርቆስማቴዎስኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርዮሐንስ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ፍልስፍናየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትታንዛኒያኩሻዊ ቋንቋዎችጣልያንዳንቴ አሊጊዬሪምስራቅ ጎጃም ዞንሌባነብርደራርቱ ቱሉዋናው ገጽሀመርጃቫስዕልየተባበሩት ግዛቶችሽሮ ወጥማንጎኦሮሚያ ክልልዓርብትምህርትእስልምናክርስትናጆሮ ጠቢ በሌለበትም ዘንድ ጠብ ጸጥ ይላልቴሌብርባህር ዛፍሥላሴጅቡቲ (ከተማ)አልባኒያጋምቢያሲዳማቦትስዋናወሎገብርኤል (መልዐክ)መጽሐፈ ሶስናመርየም የእየሱስ (አ.ሰ) እናትየሮማ ግዛትይሖዋአክሊሉ ሀብተ-ወልድጀጎል ግንብገበያየዊኪፔዲያዎች ዝርዝርየአፍሪካ ኅብረትንፍሮመናፍቅቢ.ቢ.ሲ.ዳግማዊ አባ ጅፋርውሃጋናጫትኤድስዮሐንስ ፬ኛፍቅርመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስመሐሙድ አህመድፋሲለደስጋብቻሀጫሉሁንዴሳአክሱም ጽዮንኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንአዋሽ ወንዝሐመልማል አባተአዳም ረታየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችፈረንሣይንጉሥህግ ተርጓሚ1967ታምራት ደስታአራት ማዕዘንገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችፍልስጤምመቀሌቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴአማራ (ክልል)ታሪክጅቡቲአፄ🡆 More