አጋታርከስ

አጋታርከስ (Ἀγάθαρχος) ወይንም (Ἀγαθαρχίδης) ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለተኛው ክፍለ ዘመን (200-130 ዓ.ዓ.) ይኖር የነበር የግሪክ መልክዓ ምድር ተመራማሪ ነበር። ግሪክ ውስጥ ናይደስ እምትባል ቦታ የተወለደው አጋርታከስ በኋላ ወደ አሌክሳንድሪያ ሄዶ ግብጽ ውስጥ እንደኖረ ታሪኩ ይገልጻል። በግብጽ ህይወቱ ውስጥ መጀመሪያ አስተማሪነት ቢቀጠርም በኋላ ግን የሄራክሊደስ ጸሐፊ ለመሆን በቃ። ሄራክሊደስ እንግዲይ የቶሎሚ 6ኛ ወዳጅ የነበረና በኋላ ከአንጾክዮስ ጋር በተደረገው ጦርነት ወደ ሶሪያ አምባሳደር ሆኖ የተሾመ ነው። በሁለቱ ጦረኞች መካከል የሰላም ድርድር ሲደረግ ሄራክሊደስ ተካፋይ ስለነበር የአጋርታከስ የጠለቀ ዕውቀት በዚህ ጊዘ ከነበረው መረጃዎችን የመፈተን ዕድል ይመነጫል። ሆኖም በኋላ ቶሎሚ 8ኛ ሲነግስ ማናቸውም በቶሎሚ 6ኛ ጥቅም ያገኙ ጠቢባን እንዲሰደዱ እንጂ እንዳይጠቀሙ አዋጅ ወጣ። ስለሆነም አጋርታከስ እና ሌሎች ተማሪዎች ለብዙ ዘመን ከኖሩባት አሌክሳንድሪያ እንዲሰደዱ ሆነ።

ስራዎች

አጋርታከስ ብዙ ሰፊና ትላልቅ ጽሑፎችን አቅርቧል። ለዚህ መሰረቱ በሄራክሊደስ አማካይነት የንጉሱን መዝገብ ቤት ፋይሎች ለመመርመር ስለቻለ እንደሆነ ግምት አለ። ከስራዎቹ ውስጥ የእስያ ታሪክ (10 መጻሕፍት)፣ የአውሮጳ ታሪክ (49 መጻሕፍት)፣ እና ስለ ቀይ ባሕር (5 መጻሕፍት) የተሰኙት ተጠቃሽ ናቸው። ከስራዎቹ ስፋትና ጥልቀት አንጻር በኋላ ለተነሱ ብዙ የመልክዓ ምድር እና ታሪክ ጸሐፍት መሰረት በመሆን አገልግሏል። ምንም እንኳ በአሁኑ ዘመን አብዛኛወቹ የአጋርታከስ ስራዎች የጠፉ ቢሆንም በጥንቱ ዘመን ጽሑፎቹ በብዛት የተሰራጩ እንደነበር ይገመታል። ከድዮዶረስ ሴኩለስ እስከ ፖዚዶኒዮስ ድረስ የአጋርታከስ ስራቸው በሰፊው ይገኙባቸዋል። ታሪክንና ፍልስፍናን አቀናጅቶ ለማቅረብ የሞከረበት ስራውም በፖይዚዶኒዮስ ዘንድ ተቀባይነትንና ቀጣይነትን ያገኘ ነበር።

Tags:

አሌክሳንድሪያግብጽ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ግራኝ አህመድንግሥት ኤልሣቤጥ ዳግማዊትገብረ ክርስቶስ ደስታመንፈስ ቅዱስሰንጠረዥየኮንሶ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ኅብረትገረማቁንዶ በርበሬፈረንሳይኛአልጋ ወራሽፍቅርየማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላትሥርዓተ ነጥቦችሙሴጫትፈሊጣዊ አነጋገር ወግመልአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭባህሩ ቀኜጳውሎስ ኞኞሥነ ጥበብሙዚቃእግዚአብሔርእቴጌ ምንትዋብአባይፖሊስኃይሌ ገብረ ሥላሴጥቁር አባይመሀንዲስነትየጣሊያን መንግሥት (1861–1946 እ.ኤ.አ.)ናይሎ ሳህራዊ ቋንቋዎችሰዋስውእሸቱ መለስየፀሐይ ግርዶሽሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥትስፖርትየኢትዮጵያ ካርታ 1690ነፍስጥቁር ቀዳዳበላይ ዘለቀአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነትሥነ ፈለክላሊበላክራር771 እ.ኤ.አ.ወረቀትወርቃማው ሕግአንበሳየሲዳማ ባሕላዊ ሐይማኖትኢት ቋንቋእየሩሳሌምአቃቂ ቃሊቲቁጥርአምልኮየኢትዮጵያ ካርታ 1936ስሜን አሜሪካቀለምበዓሉ ግርማየሕግ የበላይነትፈንገስLቶማስ ኤዲሶንዛጔ ሥርወ-መንግሥትየቀን መቁጠሪያባህርአለማየሁ እሸቴኢያሱ ፭ኛኣበራ ሞላጤና ኣዳም«የሰብዓዊ መብት አቀፋዊ መግለጽ»ተድባበ ማርያም🡆 More