ቶክ ፒሲን (Tok Pisin) በስሜን ፓፑዋ ኒው ግኒ የሚናገር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲቃላ ነው። ከእንግሊዝኛ ስዋሰው በጣም ተለውጧልና ዛሬ እንደ ራሱ ቋንቋ ይቆጠራል። የፓፑዋ ኒው ግኒ መደበኛ ቋንቋ ሆኖ በ120,000 ያሕል ተናጋሪዎችና በ4 ሚሊዮን እንደ 2ኛ ቋንቋ ይነገራል።
የቶክ ፒሲን አጀማመር በፓሲፊክ ውቅያኖስ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ የተላያዩም ልሣናት የሚችሉ ሰራተኞች አንድላይ ለአትክልት ስፍራዎች ሲሰሩ ነበር። ብዙ ጊዜ የእነዚህ ሰራተኞች የጋራ ቋንቋ ጥቂት ቀላል እንግሊዝኛ ቃሎች ብቻ ነበር። ስለዚህ አዲስ "የቋንቋ ዲቃላ" ተወለደ። ከእንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከደሴተኞቹ ቋንቋዎች፣ ከጀርመንኛ፣ ወይም ከፖርቱጊዝ ነበር። ይህ ቋንቋ "ፕጅን" ተብሎ አሁን ሶስት ተወላጆች አሉት፣ እነሱም ቢስላማ (በቫኑዋቱ) ፒጂን (በሰሎሞን ደሴቶች) እና ቶክ ፒሲን ይባላሉ። ቶክ ፒሲን በአንዳንድ ትምህርት ቤት የትምህርት ቋንቋ ነው።
ነጠላ | ቢጥ | ብዙ | |
---|---|---|---|
1ኛ | ሚ (እኔ) | ሚቱፔላ (ሁለታችን) | ሚፔላ (እኛ) |
2ኛ | ዩ (አንተ፣ አንቺ) | ዩቱፔላ (ሁለታችሁ) | ዩፔላ (እናንተ) |
3ኛ | ኤም (እሱ፣ እሷ) | ቱፔላ (ሁለታ) | ኦል (እነሱ) |
የአባታችን ጸሎት፦
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ቶክ ፒሲን, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.