የአውስትራሊያ ንጉሣዊ በራሪ ሐኪም አገልግሎት

የአውስትራሊያ ንጉሣዊ በራሪ ሐኪም አገልግሎት (Royal Flying Doctor Service ወይም ባጭሩ Flying Doctor በራሪ ሐኪም) ከ1928 እ.ኤ.አ.

ጀምሮ በአውስትራሊያ ሰፊ ምድረ በዳ በአውሮፕላን የሚዘዋወር የሕክምና አገልግሎት ነው።

የአውስትራሊያ ንጉሣዊ በራሪ ሐኪም አገልግሎት
የRFDS አውሮፕላን ማቆሚያ

መጀመርያ በ1928 እ.ኤ.አ. «የአውስትራሊያ ምድረገብ ሚስዮን አየራዊ ህክምና አገልግሎት» (Australian Inland Mission Aerial Medical Service) ተብሎ በፕሮቴስታንት ሰባኪና የአውትራሊያ ምድረገብ ሚስዮን መስራች ክቡር ጆን ፍሊን ተመሠረተ። በ1934 እ.ኤ.አ. ስሙም «የአውስትራሊያ አየራዊ ሕክምና አገልግሎት» (Australian Aerial Medical Service) ሆነ። በ1942 እ.ኤ.አ. ደግሞ ስሙ እንደገና ተቀይሮ «በራሪ ሐኪም አገልግሎት» (Flying Doctor Service) ተባለ። በ1955 እ.ኤ.አ. በንግሥት እልሳቤት ጥብቅና ድጋፍ በይፋ «ንጉሣዊ» (Royal) ተጨምሮ ተሾመ።

ብዙ ሆስፒታሎች ሊቆሙበት ባልተቻላቸው በአውስትራሊያ ምድረ በዳ ለሚገኙት በሽተኞች፣ በራሪ ሐኪሞች በአየር ይደርሳሉ። መድኃኒትና ህክምና ከማቅረባቸው በላይ በሽተኛውን ደግሞ ወደ ሜዳ ሆስፒታል ሊያደርሱ ይችላሉ።

ብዙ የቴሌቪዥን ትርዒቶች የበራሪ ሀኪሞችን ኑሮ አብራረዋል፣ ከነሱም The Flying Doctor (1959-60 እ.እ.አ.)፤ The Flying Doctors (1986-93 እ.እ.አ.)፤ R.F.D.S. (1993-94 እ.እ.አ.)፤ RFDS: Royal Flying Doctor Service (2021 እ.እ.አ.-አሁን) ፣ እንዲሁም ፊልሙ The Flying Doctor በ1936 እ.እ.አ. ተሠራ።

Tags:

አውስትራሊያ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ኢትዮጵያድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳየኢትዮጵያ ሙዚቃደብረ አቡነ ሙሴኢንዶኔዥያየቻይና ሪፐብሊክቤት (ፊደል)ተረትና ምሳሌእዮብ መኮንንቅፅል1944ጋብቻኪርጊዝስታንተሳቢ እንስሳክርስቶስ ሠምራባክቴሪያሕገ መንግሥትማርስሚስቶች በኖህ መርከብ ላይእሳት ወይስ አበባአሦርየጋብቻ ሥነ-ስርዓትሙሴኤቨረስት ተራራዐቢይ አህመድተምርገና12 Juneአዶልፍ ሂትለርነፋስ ስልክሐረርመጽሕፍ ቅዱስየቃል ክፍሎችቅዱስ ራጉኤልመጽሐፈ ሄኖክኦሪት ዘፍጥረትሥነ ንዋይዓረፍተ-ነገርግዕዝጎጃም ክፍለ ሀገርሥነ ጥበብዶሪየዔድን ገነትይስሐቅህብስት ጥሩነህኦሞ ወንዝኮምፒዩተርየሉቃስ ወንጌልፋሲካኤሌክትሪክ ምድጃ ፡ እራስህ ስራወተትየሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት ሲርብ የበሉት ነውፍቅር በዘመነ ሽብርወልቂጤቭላዲሚር ፑቲንድንችእየሩሳሌምፒያኖDቤንችጠጅአበበ ቢቂላጅቡቲራስ ዳርጌብጉንጅአክሱም ጽዮንበዓሉ ግርማሸዋመልክዓ ምድርደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅንአክሱምእስራኤልቅድስት አርሴማስልክ🡆 More