የሲቢሊን ራዕዮች በግሪክ የተጻፉ በ12 መጻሕፍት ተከፋፍለው የትንቢት ግጥሞች ክምችት ናቸው። እነሱ የሲቢል (ሴት ነቢይ) ሥራ ናቸው ይላሉ። ይሁንና የዛሬ ሊቃውንት እኚህ ትንቢቶች በአይሁዶች ወይም በክርስቲያኖች ተጽፈው ዕውነተኛ የሲቢሊን መጻሕፍት ሊሆኑ አይችሉም ባዮች ናቸው። ትንቢቶቹ የተባሉ ከድርጊቶቹ በኋላ ተነበዩና ከ2ኛው መቶ ዘመን ዓክልበ እስከ 6ኛ መቶ ዘመን ከክርስቶስ በኋላ መጻፍ ነበረባቸው ሲሉ ይክራክራሉ። ምክንያቱም ከትንቢቶቹ መኃል ብዙዎች ስለ መሢህ ወይም ስለ ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ ነክ ጉዳይ የሚነበዩ ናቸው። ለሎችም ደግሞ ስለ ሮማ መንግሥት ዕድልና ታሪክ ስለሚነበዩ ስለዚህ ከድርጊቶቹ በኋላ መነበይ ነበረባቸው ይላሉ የዛሬው ምሁራን።
ቢሆንም እነዚህ መጻሕፍት የአይሁድና የክርስትና ሃይማኖት ነክ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን ከግሪክና ከሮማ አረመኔ ሃይማኖት የተለቀሙ ብዙ ስሞች ወይም ሃሳቦች ይገኙባቸዋል። ለምሳሌ ከግሪክ ጸሐፊዎች ሆሜርና ሄሲዮድ፣ እንዲሁም ከብሉይ ኪዳን ስለ ኤደን ገነት ስለ ኖህና ስለ ባቢሎን ግንብ የሚል ወሬ አለባቸው።
በጥንት የታወቁት 'ሲቢሊን መጻሕፍት' በሮማ ከተማ በቤተ መቅደስ ይጠበቁ ሲሆን በ90 አመት ዓክልበ በእሳት ተቃጠሉ። ስለዚህ የሮማ ላይኛ ምክር ቤት (ሴናት) በ84 ዓክልበ ተልእኮዎች ተመሳሳይ ትንቢቶች አገኝተው እንዲተኩ ላኩዋቸው። ከዚያ እስከ 397 ዓ.ም. ቆዩ። በዚያን ጊዜ የአሪዮስ ክርስትና ትምህርት አራማጅ የሆነ ስቲሊኮ እንዳቃጠላቸው ይባላል። ነገር ግን ስለ ይዞታቸው ብዙ አይታወቅምና ከሚታወቁት 'ሲቢሊን ራዕዮች' ጋር አንድላይ አይሆኑም ብለው ምሁራን ይገመታሉ።
አንድ ክርስቲያን ፈላስፋ አቲናጎራስ አቴናዊው ክርስቲያኖች በአረመኔ ሮማ መንግሥት በተሠቃዩበት ወቅት በ168 ዓ.ም. ወደ ቄሣር ማርቆስ አውሬሊዮስ 'አቤቱታ ለክርስቲያኖቹ' ሲጽፍ ከነዚህ ዛሬም እውቅ ከሆኑት ንግሮች ቃል ለቃል በሰፊ መጥቀሱ እርግጠኛ ነው። የጠቀሳቸው ከነሆሜርና ሄሲዮድ ጋር ሲሆን ብዙ ጊዜ 'እነዚህ መጻሕፍት ሁሉ ለቄሣር ታዋቂ ናቸው' ብሎ ጻፈ። በዚህ ጊዜ መጻሕፍቱ በሮማ ገና ይገኙ ነበርና ስለዚህ ምናልባት ከሲቢሊን ራዕዮች አንዳንድ ትክክለኛ እንደ ሆነ ይቻላል።
ሌሎች የክርስትና አባቶችና ሃዋርያት ደግሞ የሲቢሊን ራዕዮችን ጠቀሱ። ቴዎፊሎስ ዘአንጾኪያ የአንጾኪያ ጳጳስ (170 ዓ.ም. አካባቢ) ቀለምንጦስ ዘእስክንድርያ (190 ዓ.ም. አካባቢ) ላክታንትዮስ (295 ዓ.ም. አካባቢ) እና ቅዱስ አውግስጢኖስ (390 ዓ.ም. አካባቢ) ሁላቸው ጠቅሰዋቸዋል ። ዩስቲኑስ ሰማዕት (140 ዓ.ም. አካባቢ) ደግሞ አንዳንድ የሱማይ ሲቢል ትንቢቶች ጠቅሰዋል። ይህ ጥቅስ ግን ዛሬ በሚታወቁት ንግሮች መሓል አይገኝም።
የሚከተለው ታዋቂ ጥቅስ የባቢሎን ግንብን ታሪክ ይመስላል።
ከሶስተኛው መጽሐፍ መስመሮች 119-147፦
(III: 119-147)
(III: 1004-1031) - ሲቢሊቱ ስለ ራሷ ታሪክ የምትለው:-
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article የሲቢሊን ራዕዮች, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.