ለእንስሳ ዝርያ፣ ቆርኬን ይዩ።
ቆርኪ የኢትዮጵያ ህጻናት ከድንጋይና ከቆርኪ የሚጫወቱት ጨዋታ ነው። ቆርኪ ደግሞ የመጠጥ ጠርሙሶች የቆርቆሮ መክደኛ ነው። ይህ ጨዋታ ብዙን ጊዜ በልጆች የሚተገበረው በክረምት ወቅት ትምህርት ቤት ሲዘጋ ነው። ብዙ አይነት የቆርኪ ጨዋታወች አሉ።ከእነሱ ውስጥ ዲሞ፣ጉርጌ፣ዋንጫ ወዘተ. የሚጠቀሱ ሲሆን በአብዛኛው ሁሉም ቆርኪን በመደርደር ከቆርኪው በመራቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ በመጣል ድንጋዩን አርቆ የጣለው/ጣለቸው የመጀመሪያ እድሉን ይወስድና የተደረደረውን ቆርኪ ለመምታት ይሞክራል። በመታቸው ቆርኪዎች ልክም ይሰበስባል ማለት ነው። ብዙ ቆርኪዎችን የሰበሰበ ወይም በልጆች ቋንቋ የበላ የጫዋታው አሸናፊ ይሆናል። የቆርኪ ጨዋታ ፉክክርን፣ እቅድ ማውጣትን፣ ስልት አወጣጥና አተገባበርን ለህጻናት ያስተምራል።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ቆርኪ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.