ሳንኮሬ ማድራሣ

ሳንኮሬ ማድራሣ በቲምቡክቱ፣ ማሊ መንግሥት፣ ከ981 እስከ 1585 ዓም ያህል የቆየ የእስልምና መስጊድና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወይም ዩኒቨርሲቲ ነበረ። ከቲምቡክቱ ዩኒቨርሲቲ ሦስት ተቋማት መጀመርያው የተመሠረተው ነበር።

ሳንኮሬ ማድራሣ
ሳንኮሬ ማድራሣ፣ ቲምቡክቱ፣ ማሊ

መስጊዱ የተመሠረተው በ981 ዓም በቲምቡክቱ ዳኛ በአል-ቃዲ አቂብ ነበረ። ከ1100 ዓም ያህል በፊት በአንዲት ሀብታም ማንዲንካ ወይዘሮ እርዳታ፣ ሕንጻው ሰፊ ማድራሣ (ተቋም) ሆነ። ያንጊዜ የአውሮፓ ትልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ገና ምንም ሳይኖሩ፣ ለአፍሪካ ከፍተኛ ደረጃ ተማሮች ግን የእስላም ማድራሦች በቲምቡክቱ፣ በካይሮ እና በሞሮኮ ተገኝተው ነበር።

በ1200 ዓም ግድም የተማሮች ቁጥር 25,000 ነበር፤ የከተማውም ሕዝብ ቁጥር ያንጊዜ 100,000 ነበር። በተለይ ከ1300 ዓም በኋላ በጣም ስመ ጥሩ ትምህርት ተቋም ሆነ።

የተቋሙ መደበኛ ቋንቋ አረብኛ ነበር። በተማሮች መጀመርያ ዓመት ቁራኑን ሙሉ በአረብኛ ከልብ መዳግም ነበረባቸው። ዋና የጥናት ዘርፎች እስልምና፣ ቁራንሕግሥነ ጽሑፍ ነበሩ። በተጨማሪ ሕክምና፣ ቀዶ ጥገና፣ ሥነ ፈለክትምህርተ ሂሳብየተፈጥሮ ሕግጋት ጥናትየጥንተ ንጥር ጥናትፍልስፍናየቋንቋ ጥናትመልክዓ ምድርታሪክሥነ ጥበብ ጥናቶች አስተማሩ። ከዚያ በላይ ተማሮች ንግድ ወይም ሙያ ይማሩ ነበር፦ አናጢነት፣ ግብርና፣ አሣ ማጥመድ፣ ግንባታ፣ ጫማ መሥራት፣ ልብስ ሰፊነት፣ ወዘተ. ይማሩ ነበር።

በ1319 ዓም ሁለተኛ ማድራሣ ጂንገሬ በር ተቋም ተሠራ፤ በ1392 ዓም ሦስተኛው ተቋም ሲዲ ያህያ ተሠራ ። እነዚህ ሦስት ማድራሦች፣ ሳንኮሬ፣ ጂንገሬ በር እና ሲዲ ያህያ፣ አንድላይ የቲምቡክቱ ዩኒቨርሲቲ ይባሉ ነበር። በ1460 ዓም ቲምቡክቱ ከማሊ መንግሥት ወደ አዲሱ ሶንግኃይ መንግሥት ዓለፈ። በ1585 ዓም ግን የሞሮኮ ወራሪ ሃያላት ማድራሦቹን አጠፉ፣ ብዙ መጻሕፍት ቤቶችንም አቃጠሉ። ቢሆንም ከማድራሣው 70,000 ያህል ሰነዶች እስካሁን ተርፈዋል፣ ዛሬም እየተነተኑ ነው።

ዝነኛ አስተማሮች፦

  • አህማድ ባባ አል-ማሡፊ (1549-1619 ዓም) የተቋሙ መጨረሻው መሪ፣ 60 መጻሕፍት ጽፈው ነበር። ሞሮካውያን ወደ ስደት ላኩት።
  • ሞሐመድ ባጋዮጎ (1515-1585) ፋላስፋ፣ ጸሐፊና መምህር፣ በሞሮካውያን ተገደለ።

Tags:

እስልምና

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

አቡጊዳየሲዳማ ባሕላዊ ሐይማኖትበጌምድርህሊናኦሪት ዘኊልቊዳዊት1965ኮምፒዩተርማንችስተር ዩናይትድከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርየሥነ፡ልቡና ትምህርትቦሌ ዓለም አቀፍ ጥያራ ጣቢያፕሉቶጋስጫ አባ ጊዮርጊስጳውሎስ ኞኞመጽሐፈ ሶስናአስቴር አወቀዋቅላሚየኢትዮጵያ ሙዚቃተውሳከ ግሥታራንግድቅዱስ ራጉኤልበ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትሱፍአሊ ቢራሥርዓት አልበኝነትተመስገን ተካድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳሥነ ምግባርየኢንዱስትሪ አብዮትንቃተ ህሊናአዲስ ኪዳንካናቢስ (መድሃኒት)አርበኛሲ (የኮምፒዩተር ፍርገማ ቋንቋ)ታምራት ደስታሸዋሩሲያየኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርየሰራተኞች ሕግሆሣዕና በዓልወልቂጤጌዴኦመጽሐፍ ቅዱስየኖህ ልጆችግሽጣአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስራያቅኝ ግዛትመሠረተ ልማትይኩኖ አምላክደቡብ ቻይና ባሕርጀርመንሚስቱን ገድሎ አማቱ ቤት ተሽሽገአማርኛ ልብ ወለድ መፃህፍትገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችአቡነ ባስልዮስምሳሌየጋብቻ ሥነ-ስርዓትባሕልአፄየአዲስ አበባ ከንቲባአዳልደጃዝማችግዝፈትእርሳስቢስማርክታጂኪስታንጠላኩሻዊ ቋንቋዎችጸሎተ ምናሴ🡆 More