ሞሮኮ (አረበኛ፡ المغرب) በሰሜን-ምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝና በሕገ-መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓት የምትተዳደር የ፴፪ ሚሊዮን ሕዝብ አገር ናት። መግሪብ በምዕራብ ድንበሯ የአትላንቲክ ውቅያኖስ፤ በሰሜን የሜድትራኒያን ባሕር፤በምሥራቅ አልጄሪያ እና በደቡብ ምዕራባዊ ሣህራ ታዋስናለች። የመግሪብ ርዕሰ ከተማ በአገሪቱ በስተ ምዕራብ የምትገኘውና በሕዝብ ብዛት ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ራባት (አማርኛ፡ ርባጥ]] ስትሆን የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሁም የአገሪቷ ታላቅ የባሕር ወደብ የሚገኝባት የካዛብላንካ ከተማ እና ጥንታዊቷ ማራኬሽ (አማርኛ፡ ምራክሽ) ሌሎቹ ትላልቅ ከተሞች ናቸው።
المملكة المغربية | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
| ||||||
ብሔራዊ መዝሙር: "لله، الوطن، الملك" | ||||||
ዋና ከተማ | ራባት | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ዓረብኛ | |||||
መንግሥት ንጉሥ ጠቅላይ ሚኒስትር | ፓርለሜንታዊ ንጉሳዊ አገዛዝ ንጉሥ ሙሐመድ ሳድሳዊ ሳደዲን ኦጥማኒ | |||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) | 446,550 (57ኛ) 0.056 | |||||
የሕዝብ ብዛት የ2017 እ.ኤ.አ. ግምት የ2014 እ.ኤ.አ. ቆጠራ | 34,422,600 (39ኛ) 33,848,242 | |||||
ገንዘብ | ድርሃም | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +0 | |||||
የስልክ መግቢያ | +212 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .ma |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ሞሮኮ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.