አረንጓዴ ዋቅላሚዎች ሰፊ የሆነ ኢመደበኛ የዋቅላሚዎች መደብ ነው። በውስጡ አሁን በተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙትን ክሎሮፋይታንና ካሮፋይታን የሚያቅፍ ነው።
አረንጓዴ ዋቅላሚዎች በአብዛኛው ሁለት ልምጭት ያላቸው አንድህዋሴ እና ኩይዋሳዊ ባለልምጭት ዝርያዎችን፣ የተለያዩ ኩይዋሳዊ፣ ድቡልቡል እና ዘሃዊ ቅርፅ ያላቸው ዝርያዎችን እንዲሁም ትላልቅ ባለብዙ ህዋስ የባህር አረሞችን ያካትታሉ፡፡ ብዛታቸው ወደ 22,000 ገደማ የሚሆኑ የአረንጓዴ ዋቅላሚ ዝርያዎች አሉ፡፡
አረንጓዴ ዋቅላሚዎች በታይላኮይድ ድርድር ውስጥ ደማቅ አረንጓዴ ቀለም የሚሰጧቸውን ኤ እና ቢ የተሰኙ አረንጓዴ ሐመልሚሎችን እንዲሁም ተጨማሪ ቀለማት ቤታ ካሮቲን (ደማቅ ብርትኳናማ)እና ዛንቶፊሎች (ቢጫ) ቀለም ያቀፈ አረንጓቀፍ አላቸው።
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article አረንጓዴ ዋቅላሚዎች, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.