በጀት

በጀት ማለት ለወደፊቱ የሚመጣን ገቢና ወጪ የሚተነብይ የንዋይ/ገንዘብ እቅድ ነው። በዚህ እቅድ ውስጥ ቁጠባ፣ ብድር እና ወጪ ይካተታሉ ። ግለሰቦች ወይንም ቢዝነሶች ገቢና ወጪያቸው ሲመረመር ከሞላ ጎደል ቋሚ ሆኖ ስለሚገኝ የበጀት ጥቅም ከዚህ ይመነጫል። ማለት፣ ቋሚ ገቢ ወጪ፣ ለወደፊት ይሚሆነን ለመተንበይ አመቺ ነው። ተንብዮ በበጀት መመራት ግለሰቦብ በገንዘባቸው/ንዋያቸው ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ያደርጋል። አላስፈላጊ ወጭወችን ለመለየት እና በአቅም መኖርን ለማወቅ ይረዳል።

የበጀት አሰራር

ቅድሚያ መሰረት

በጀት ምሳሌ
የወር ገቢ
የተተነበየ ተጨባጭ ልዩነት
ደመወዝ - ከስራ ፩ 200 185 -15
ደመወዝ - ከስራ ፪ 400 410 +10
ሌሎች የገቢ ምንጮች 60 50 -10
የወሩ አጠቃላይ ገቢ 660 645 -15
የወር ወጪ
የተተነበየ ተጨባጭ ልዩነት
ሞርጌጅ/ኪራይ 300 300 0
መኪና ኢንሹራንስ 50 50 0
ክሬዲት ካርድ 50 60 +10
ሴቪንግ አካውንት 50 50 0
ምግብ 100 90 -10
የወሩ አጠቃላይ ወጪ 550 550 0

በመጀመሪያ ደረጃ ላለፉት ሁለት ወራት የነበረን የወጪ ዓይነቶች ማወቅ ያስፈልጋል። እማይታወቅ ከሆነ ከአሁኑ በመጀመር ለሁለት ወራት መመዝገብ መልካም ልማድ ነው።

ለአንድ ወር እያንዳንዷን ወጪ ከላይ በተቀመጠው የበጀት ዓይነት መሰርት መመዝገብ ጥሩ ምክር ነው።

የወር ደሞዝን ወይንም ሌላ አይነት ገቢን ለብቻው ማስላት፣ ሁለተኛው የበጀት አሰራር ደረጃ ነው።

ከዚያ በኋላ፣ ወጪን ከገበሚ መቀነስና ውጤቱ ነጌቲቭ ከሆነ ያለ አቅም መኖርን ስለሚያመላክት ለወደፊት ይህ እንዳይሆን የወጪ ልማድን እንዴት ማስተካከል እንዳለብን ዘዴ መዘየድ።

ውጤቱ ፖዚቲቭ ሆኖ ከተገኘ ግን ያለ ገቢ ከወጪ ስለሚበልጥ ተራፊውን ገንዘብ በየወሩ ወደ ሴቪንግ አካውንት ማስተላለፍ ጥሩ ተግባር ነው።

ድህረ በጀት

በየወሩ በጀቱ መጻፍና መመርመር ይኖርበታል ማለት ነው። ለየጊዜው እንዲስማማ ተደርጎ መሻሻልና መታደስም ይኖርበታል። ወጭና ገቢ በሂደት በሚገባ ከታወቀ በኋላ የወደፊቱን ማቀድ ቀላል ይሆናል። ወጪን ለመቀነስ ወጭን በዝርዝር ጽፎ በዚያ ዝርዝር መሰረት መመራት ከአላስፈላጊ ወጪ ያድናል።

ዕዳና በጀት

የበጀት ዋናው ጥቅም አንድ ግለሰብ በራሱ ገቢና ወጪ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረው ማስቻሉ ነው። ስለሆነም ግለሰቦች ዕዳ ውስጥ መግባት ሲጀምሩ በቶሎ እንዲያውቁ ይሆናሉ። ስለሆነም ችግሩ ከመባባሱ በፊት አስቀድመው እርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ።

አንድ ግለሰብ ዕዳ ውስጥ እየገባ መሆኑን መረዳት ሲጀመር መጀመሪያውኑ የዕዳውን አይነት መለየት አስፈላጊ ነው። ቅድሚያ ትኩረት አግኝተው መከፈል ያለባቸው እማይለወጡ ዕዳወች (ምሳሌ ሞርጌጅ፣ የቤት ኪራይ ..) እና ቀስ ብለው ሊከፍሉ የሚችሉ ተለዋዋጭ ዕዳዎች (ምግብ፣ የኤሌክትሪክውሃ ና ሌሎች በጥንቃቄ ሊቀነሱ የሚችሉ ቢሎች) ተለየተው ሊታወቁ ይገባል።

ዕዳዎቹ ከተለዩ በሗላ፣ ዕዳዎቹን ለማስወገድ መንገድ ማበጀት ተገቢ ነው። ለዚህ ተግባር እንዲረዳ «በደህና ጊዜ» በትንሽ በትንሹ ማጠራቀም ጥሩ ነው። ነገር ግን ይህ ተደርጎ ካልሆነ፣ ቀሪ እዳን ቀስ በቀስ ለመክፍል የሚያስችል ስምምነት ከዕዳ-ሰጪው ጋር መግባት ጥሩ ነው። ባንኮች የአንድ ግለሰብ ዕዳ ባለቤት ከሆኑ፣ ግለሰቡን ለመርዳት ፍላጎት ይኖራቸዋል፣ ምክንያቱም ከርሱ ነውና ገንዘብ የሚያገኙት። ለዚህ ተግባር እንዲረዳ ኮንሶሊዴሽን (ሁሉን ዕዳን በአንድ ላይ መሰብሰብ) እና ሪፋይናንሲንግ (ብድርን፣ በተራዘመ ጊዜ እንዲከፍሉ ማስቻል) የሚባሉ ሁለት መሳሪያወችን ባንኮች ይጠቀማሉ። እኒህን ማግኘት እዳ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ ይረዳሉ። ሆኖም እኒህ እድሎች ካልተገኙ ዴቢት ስፔሻሊስት የተሰኙ መካሪዎችን ማነጋገር ይቻላል።

ማጣቀሻ

ተጨማሪ ንባብ

Tags:

በጀት የ አሰራርበጀት ማጣቀሻበጀት ተጨማሪ ንባብበጀት

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

ዩ ቱብኢሳያስ አፈወርቂሚካኤልጥሩነሽ ዲባባዮሐንስ ፬ኛሥርዓተ ነጥቦችመርካቶኢትዮጲያአቡጊዳአክሱም ጽዮንሸለምጥማጥቀልዶችየነፃ ግዛቶች ኮመንዌልዝትምህርትባህረ ሀሳብሸዋበርእንጀራድሬዳዋዋሽንትአሸንድየትዝታብጉንጅጸጋዬ ገብረ መድህንኤሊቢስማርክሌዊሀዲስ ዓለማየሁቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴዓረፍተ-ነገርሚስቱን ገድሎ አማቱ ቤት ተሽሽገሚልኪ ዌይቦትስዋናወርጂሀይሉ ዲሣሣቡልጋመንግሥተ አክሱምተምርመልክዓ ምድርይርዳው ጤናውባሕላዊ መድኃኒትቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለችፋሲል ግምብሲ (የኮምፒዩተር ፍርገማ ቋንቋ)የሲስተም አሰሪለንደንወንጪውድድርሀይቅአበበ ቢቂላጸሎተ ምናሴሕግ ገባየመጀመሪያው የዓለም ጦርነትሲዲምግብአስርቱ ቃላትቤተ መርቆሬዎስየኢትዮጵያ ብርአሕጉርሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትዓለም-አቀፍ መደበኛ የመጽሐፍ ቁጥርመስተዋድድዱባይየጋብቻ ሥነ-ስርዓትሳክሶፎንየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርየኢትዮጵያ ካርታ 1690ሜታ (ወረዳ)12 Juneየእብድ ውሻ በሽታኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክቁጥርዓሣ🡆 More