ቅጽል - ዓይነትንና ግብርን፣ መጠንንም ለመግለጽ በስም ወይም በተውላጠ ስም ላይ የሚጨመር ቃል ቅጽል ይባላል። ስሙ እንደሚያመለክተው ቅጽል ማለት ቅጥያ ወይም ተጨማሪ ማለት ነው።
ይህ መጣጥፍ ከተመሳሳዩ መጣጥፍ ከቅፅል ጋራ እንዲዋሐድ የሚል ሀሣብ ቀርቧል። (ውይይት) |
ምሳሌ - ጥቍር ፈረስ፣ ብርቱ ፈረስ፣ ዐጭር ፈረስ።
እነሆ! ቅጽል የተባሉት "ጥቍር፣ ብርቱ፣ ዐጭር" ናቸው። ፈረስ የአንድ እንስሳ ስም ነው። ጥቍር ፈረስ ሲል ዓይነቱን፤ ብርቱ ፈረስ ሲል ግብሩን፤ ዐጭር ፈረስ ሲል መጠኑን የቅጽሉ ቃል ያስረዳል። ስለዚህም በስምና በተውላጠ ስም ላይ እየተቀጠለ ዓይነቱን፣ ግብሩን፣ መጠኑን የሚገልጽ ቃል ሁሉ "ቅጽል" ይባላል።
"ያማርኛ ሰዋስው"፣ ፲፱፵፰ ዓ.ም፣ ከብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ቅጽል, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.