ጎትሎብ ፍሬገ (Friedrich Ludwig Gottlob Frege ) (1848 - 1925) ጀርመናዊ ፈላስፋ፣ ስነ አምክንዮ ተመራማሪ፣ እና ሂሳብ አጥኝ ነበር። ፍሬገ ከጥንቱ ግሪካዊ አሪስጣጣሊስ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የአምክንዮ ትምህርት ሙሉ በሙሉ የለወጠና ፕሪዲኬት ካልኩሉስ የተባለውን የአምክንዮ ርዕዮት አለም ያበረከት ነው። በዚህ አዲሱ አምክንዮ ስርዓት የተወሰኑ አባባሎች እንዴት በአምክንዮ እንደሚፈቱና አንድን ማረጋገጫ (proof) በርግጥ ትክክል ነው የሚባልበትን ስልት ያቋቋመ ነው። ከዚህ በመነሳት ማናቸውም የሂሳብ ርዕዮቶች ወደ ቀልል ያሉ የአምክንዮ አባባሎች እንደሚቀየሩ ማሳየት ችሏል። ምንም እንኳ አጠቃላዩን የሂሳብ ትምህርት ወደ ስነ-አምክንዮ ለመቀየር ያደረገው ሙከራ በአንዲት ያልተረጋገጠች ዕውነታ (axiom) ምክንያት በተነሳች ስርዓታዊ ቅራኔ ለውድቀት ቢበቃም ስለ ትርጉም እና ስለ ዘዴ ባቀረበው ጥናቱ ግን እስካሁን የሚሰራባቸውን እውነታወች ለማግኘት ችሏል። ስለቋንቋም ያስቀመጠው አጠቃላይ ርዕዮት እስካሁን ድረስ በፈላስፎች ሲሰራበት ይገኛል። ሆኖም ግን ህይወቱን በሙሉ ሂስባን ወደ ስነ-አምክንዮ የመቀየር ትልሙ ሳይሳካለት ቀርቷል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
This article uses material from the Wikipedia አማርኛ article ፍሬገ, which is released under the Creative Commons Attribution-ShareAlike 3.0 license ("CC BY-SA 3.0"); additional terms may apply (view authors). Content is available under CC BY-SA 4.0 unless otherwise noted. Images, videos and audio are available under their respective licenses.
®Wikipedia is a registered trademark of the Wiki Foundation, Inc. Wiki አማርኛ (DUHOCTRUNGQUOC.VN) is an independent company and has no affiliation with Wiki Foundation.