የሷሶን ግዛት

የሷሶን ግዛት በስሜን ጋሊያ (የዛሬው ፈረንሳይ አገር) የተገኘና ከሮሜ መንግሥት ውድቀት (በ468 ዓ.ም.) በኋላ ትንሽ የቆየ የሮማውያን ግዛት ነበረ።

የሷሶን ግዛት
የሷሶን ግዛት፣ በ478 ዓ.ም.

የሷሶን መንግሥት መነሻ የሮሜ ንጉሠ ነገሥት ማዮሪያኑስ በ449 ዓ.ም. አይጊዲዩስን የጋሊያ አውራጃ ዋና አለቃ እንዲሆን በሾሙበት ወቅት ሆነ።

5ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመናውያን ብሔሮች ወደ ሮሜ ግዛት እየፈለሱ ነበር፣ በተለይም ቪዚጎቶች የተባለው ትልቅ ሕዝብ ለሮሜ ሰዎች እንደ ወታደሮች ስላገለገላቸው፣ መሬት በደቡብ-ምዕራብ ጋሊያ ተሠጥተው ነበር። ብዙ ጊዜ ሳያልፍ ግን የሮማውያን ሥልጣን እየደከመ እኚህ ቪዚጎቶች በራሳቸው ንጉሥ ሥር ሆነው ግዛታቸውን ያስፋፉ ጀመር። ስለዚህ አይጊዲዩስ የተቀበለው አውራጃ በስሜን ጋሊያ ሲሆን ወደ ጣልያና ወደ ሮሜ ያገናኘው ጠባብ ስርጥ ብቻ ነበር። ይህም ስርጥ ደግሞ በማዮሪያኑስ ዘመን በጀርመናውያን ነገዶች በመያዙ፣ የአይጊዲዩስ ግዛት ያንጊዜ ከሮሜ ተቋረጠ።

ኃይለኛው ጀርመናዊ ጦር አለቃ ሪኪመር በ453 ዓ.ም. ማዮሪያኑስን ካስገደላቸው በኋላ፣ አይጊዲዩስ ሥልጣኑን በጋሊያ ጠበቀው። በ455 ዓ.ም. ከፍራንኮች ጋር ተባብሮ፣ ቪዚጎቶቹን በኦርሌያን ውጊያ ድል አደረገ። በ456 ዓ.ም. ግን አይጊዲዩስ ተገደለ፤ ልጁም ሲያግሪዩስ ግዛቱን ወረሰ። ማዕረጉ በይፋ የሮሜ አገረ ገዥ ቢሆንም፣ ጀርመናዊ ጎረቤቶቹ «የሮማውያን ንጉሥ» ይሉት ነበር። መቀመጫውም በአሁኑ ሷሶን ከተማ (በሮማይስጥኖዊዱኑም) ነበረ። ስለዚህ በአንዳንድ ታሪክ ግዛቱ «የሷሶን መንግሥት» ወይም «የሲያግሪዩስ መንግሥት» ይባላል።

በሮሜ ጣልያ በ468 ዓ.ም. መጨረሻው ንጉሠ ነገሥት ሮሙሉስ አውግስጦስ በጀርመናዊው አለቃ ኦዶዋካር ስለ ተሻሩ፣ የሮሜ ነገሥታት ሥልጣን በምዕራብ ተቋረጠ። ሲያግሪዩስ ግን የኦዶዋካርን መንግሥት ስላልተቀበለ፣ እርሱ በስሜን ጋሊያ ገዢ ሆኖ የሮሜ ሕግጋትን አስቀጠለ።

የፍራንኮች ንጉሥ 1 ቺልደሪክ በ473 ዓ.ም. ዐርፎ፣ ተከታዩ 1 ክሎቪስ የሲያግሪዩስ ጠላት ሆነና በጦርነት አገሩን በሙሉ ያዘ። በመጨረሻ የሷሶን ውጊያ (478 ዓ.ም.) ክሎቪስ ስያግሪዩስን አሸነፈ። ከዚህ በኋላ ግዛቱ ሁሉ ወደ ፍራንኮች መንግስት ተጨመረ። ሲያግሪዩስ ወደ ቪዚጎቶች ቢሸሽም፣ ፍራንኮች ዛቻ ስለ ጣሉ ቪዚጎቶች መለሱትና ይሙት በቃ ተፈረደ።

ዋቢ መጻሕፍት

የውጭ መረጃ

Tags:

ሮሜ መንግሥትፈረንሳይ

🔥 Trending searches on Wiki አማርኛ:

መሬትአጥናፍሰገድ ኪዳኔፕሩሲያየቃል ክፍሎችራስ ጎበና ዳጨ ከ1882-1889አል-ጋዛሊሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥትአዳም ረታየአድዋ ጦርነትባህር ዛፍጠላዱባይቆለጥዋናው ገጽእንቆቆየሰው ልጅሊኑክስግሥላአብዲሳ አጋስም (ሰዋስው)ጨዋታዎችትምህርትሰርቲፊኬት ኦፍ ዲፖዚትጉንዳንግስበትአረቄንጉሥላሊበላአሜሪካዎችጾመ ፍልሰታሺስቶሶሚሲስየንቅያ ጸሎተ ሃይማኖትየሰው ልጅ ጥናትውቅያኖስክርስቶስፍትሐ ነገሥትእንቆቅልሽጉግልአንሻንባርነትሀዲያደብረ ሊባኖስታንዛኒያአያሌው መስፍንዳጉሳቼክአሊ ቢራቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያቤተ አማኑኤልየዓለም የህዝብ ብዛትሚካኤልታላቁ እስክንድርስያትልየምኒልክ ድኩላኤችአይቪየሐበሻ ተረት 1899የስልክ መግቢያተስፋዬ ሳህሉሆሣዕና በዓልግዕዝ አጻጻፍአዲስ ኪዳንየልብ ሰንኮፍአውስትራልያቀነኒሳ በቀለእሸቱ መለስፋሲል ግቢንብኢየሱስቃል (የቋንቋ አካል)ያዕቆብወይን ጠጅ (ቀለም)የዓለም የመሬት ስፋትየዔድን ገነትግራኝ አህመድ🡆 More